1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የፈረንሳይ ጉብኝት 

ሐሙስ፣ ኅዳር 30 2014

ቤርቦክ የአየር ንብረት ለውጥን መከላከል በዲፕሎማሲያዊ አጀንዳቸው አጽንኦት የሚሰጡት ጉዳይ መሆኑን ከጉዞአቸው በፊት ጠቁመዋል። ቤርቦክ ከፈረንሳዩ አቻቸው ዦን ኢቭ ለድሪያን ጋር ፓሪስ ውስጥ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳሉት ከተወያዩባቸው ጉዳዮች መካከል ሁለቱ ሃገራት የሚጋሯቸው የጋራ ግቦች እና ተፈጥሮ ጥበቃ ፖሊሲ ይገኙበታል።

https://p.dw.com/p/443ns
Frankreich | Treffen Annalena Baerbock und Jean-Yves Le Drian in Paris
ምስል Gonzalo Fuentes/REUTERS

የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የፈረንሳይ ጉብኝት 

አዲሷ የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አነሌና ቤርቦክ የመጀመሪያው የስራ ጉዞአቸውን ወደ ጎረቤት ፈረንሳይ አድርገዋል። የጀርመን የቅርብ ወዳጅ ፈረንሳይን ዛሬ የጎበኙት የጀርመን የአረንጓዴዎቹ ፓርቲ መሪ ቤርቦክ ዓለማችንን ለተለያዩ ተፈጥሮአዊ ችግሮች የሚዳርገውን የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል በዲፕሎማሲያዊ አጀንዳቸው አጽንኦት የሚሰጡት ጉዳይ መሆኑን ከጉዞአቸው በፊት ጠቁመዋል። ትናንት ሃላፊነታቸውን የተረከቡት ቤርቦክ ከፈረንሳዩ አቻቸው ዦን ኢቭ ለድሪያን ጋር ፓሪስ ውስጥ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳሉት ከተወያዩባቸው ጉዳዮች መካከል ሁለቱ ሃገራት የሚጋሯቸው የጋራ ግቦች እና ተፈጥሮ ጥበቃ ፖሊሲ ይገኙበታል።ቤርቦክ ዛሬ ብራሰልና ጎረቤት ፖላንድም ነበሩ። ስለ መጀመሪያው የቤርቦክ የፓሪስ ጉብኝት የፓሪስዋን ዘጋቢያችንን ሃይማኖት ጥሩነህን በስልክ አነጋግረናታል። 


ሃይማኖት ጥሩነህ 
ኂሩት መለሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ