1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዲስ አበባ ወጣቶች ዘመቻ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 20 2013

«ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ» በሚል ርዕስ መስቀል አደባባይ በተዘጋጀዉ የሽኝት ሥርዓት እንደተገለፀዉ ከ3000 የሚበልጡ የአዲስ አበባ ወጣቶች ከሐገር መከላከያ ሠራዊት ጎን ተሰልፈዉ ለመዋጋት ይዘምታሉ። የሕክምና ቡድን አባላትም ይሳተፋሉ።

https://p.dw.com/p/3y8xh
Äthiopien l Militär wirbt um neue Mitglieder in Addis Abeba
ምስል Seyoum Getu/DW

የአዲስ አበባ ወጣቶች

ሰሜን ኢትዮጵያ ዉስጥ በሚደረገዉ ጦርነት ለመዋጋት የተመለመለመሉ የአዲስ አበባ ወጣቶች ዛሬ በይፋ ተሸኙ።  «ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ» በሚል ርዕስ መስቀል አደባባይ በተዘጋጀዉ የሽኝት ሥርዓት እንደተገለፀዉ ከ3000 የሚበልጡ የአዲስ አበባ ወጣቶች ከሐገር መከላከያ ሠራዊት ጎን ተሰልፈዉ ለመዋጋት ይዘምታሉ። በዘመቻዉ የሕክምና ቡድን አባላትም ይሳተፋሉ። በሽኝት ሥርዓቱ ላይ የመከላከያ ሚንስትር ቀነዓ ያደታ ባደረጉት ንግግር የዘመቻዉ ዓላማ «ሐገርን የማዳንና አንድነቷን የማስጠበቅ» ነዉ ብለዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በበኩላቸዉ ወጣቶቹን «ሀገርን በመከፋፋል ያሴረ የሽብር ቡድን» ባሉት ህወሓት ላይ ለመዝመት በመወሰናቸሁ ምስጋና ይገባችኋል ብለዋቸዋል፡፡ በዚሁ ሥነ-ሥርዓት ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከከተማው ነዋሪዎችና ከባለሃብቶች ሰበሰብኩ ያለውን 1,1 ቢሊየን ብር የሚገመት ገንዘብና ቁሳቁስ ለመከላከያ ሚንስቴር አስረክቧል፡፡

ስዩም ጌቱ 

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ