1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዲስ መንግስት አዋቀረ

ማክሰኞ፣ መስከረም 18 2014

የአዲስ  አበባ ከተማ አስተዳደር አዲስ መንግስት አዋቀረ።138 ቱንም መቀመጫዎች ብልፅግና ፓርቲ ያሸነፈበት የአዲስ አበባ ምክር ቤት ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ከንቲባ አድርጎ ሾሟል።ተሿሚ ከንቲባዋ አዲስ አበባን በአዲስ የፖለቲካ ባሕል እንዲጓዝ የማድረግ ኃላፊነታችንን እንወጣለን፣ ተጠያቂነትና ግልጽነት የሰፈነበት አሰራም እናዳብራለን ብለዋል።

https://p.dw.com/p/40zBA
Äthiopien Stadtbild Adis Abeba mit Schriftzug
ምስል Seyoum Getu/DW

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዲስ መንግስት አዋቀረ

የአዲስ  አበባ ከተማ አስተዳደር አዲስ መንግስት አዋቀረ
138 ቱንም መቀመጫዎች ብልፅግና ፓርቲ ያሸነፈበት የአዲስ አበባ ምክር ቤት ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ከንቲባ አድርጎ ሾሟል።
ተሿሚ ከንቲባዋ አዲስ አበባን በአዲስ የፖለቲካ ባሕል እንዲጓዝ የማድረግ ኃላፊነታችንን እንወጣለን፣ ተጠያቂነትና ግልጽነት የሰፈነበት አሰራም እናዳብራለን ብለዋል።
የከተማው ሕዝብ የከተማው ባለቤትነት ስሜቱ እንዲጠበቅለት ሊሰራ ይገባል ያሉ አስተያየት ሰጪ መስተዳድሩ ሕዝቡ የኑሮ ውድነት እንዲቃለለት፣ የአዲስ አበባ እና የኦሮሚያ ክልል የድንበር ጉዳይንም መፍትሔ ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።

ሰለሞን ሙጬ

ታምራት ዲንሳ

አዜብ ታደሰ