1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዲስ አበባ ዉዝግብ

ዓርብ፣ መጋቢት 13 2011

ምክር ቤቱ፣ «የአዲስ አበባ መስተዳድር የሕዝብ ውክልና የሌለውና ሕጋዊ አይደለም ለሚለው ትችት መልስ፣ በመሰለ መግለጫዉ «ከ5  ሚሊዮን ህዝብ በላይ ውክልና ያለው ሕጋዊ መስተዳድር ነው ብሏልም

https://p.dw.com/p/3FVe6
Äthiopien Addis Abeba
ምስል DW/S. Muchie

የአዲስ አበባ ዉዝግብ

 የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት «ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩ፣ ልዩነትን የሚያራግቡና  በመስተዳድሩ ላይ አመጽ የሚያነሳሱ» ያላቸዉ  ድርጊቶች በአስቸኳይ እንዲቆሙ አስጠነቀቀ፡፡ምክር ቤቱ፣ «የአዲስ አበባ መስተዳድር የሕዝብ ውክልና የሌለውና ሕጋዊ አይደለም» ለሚለው ትችት መልስ፣ በመሰለ መግለጫዉ «ከ5  ሚሊዮን ህዝብ በላይ ውክልና ያለው ሕጋዊ መስተዳድር ነው ብሏልም።ምክር ቤቱ ያወጣዉን ማስጠንቀቂያ በተመለከተ DW ያነጋገራቸዉ አንድ ባለሙያ  መግለጫው ሕግ ይከበር ማለቱን «ተገቢ» ብለዉታል።ይሁንና ባለሙያዉ አክለዉ እንዳሉት ምክር ቤቱ ወደ ሌላ እርምጃ ካመራ  ተቀባይነት አይኖረዉም።

 ሰለሞን ሙጬ 

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ