1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአየር ንብረት ለዉጥንና የአፍሪቃን ጥረት

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 1 2012

የአየር ንብረት ለዉጥንና ለዉጡ የሚያስከትለዉን ጉዳት ለመቀነስ ይረዳሉ የሚባሉ ጉባኤዎች፣ ዉይይቶች እና ያደባባይ ሰልፎች መደረገቸዉን በየጊዜዉ እየሰማን ነዉ። አፍሪቃ የከባቢ ዓየርን የሚበክሉ ኢንዱስትሪዎች ባይኖሯቱም የበለፀጉት ሐገራት የሚያደርሱትን ብክለት መካፈል ግድ ሆኖባታል።

https://p.dw.com/p/3UZCs
Mangroven in Kenia
ምስል DW/A. Wasike

ጤናና አካባቢ

የአየር ንብረት ለዉጥንና ለዉጡ የሚያስከትለዉን ጉዳት ለመቀነስ ይረዳሉ የሚባሉ ጉባኤዎች፣ ዉይይቶች እና ያደባባይ ሰልፎች መደረገቸዉን በየጊዜዉ እየሰማን ነዉ።የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለ25ኛ ጊዜ ያዘጋጀዉ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ባለፈዉ ሳምንት ማድሪድ-ስጳኝ ዉስጥ ሲጀመር እንደተነገረዉ ግን የዓየር ንብረት ለዉጥንና ሥጋቱን ለመቀነስ እስካሁን የተደረገዉ ጥረት ዓለምን ከስጋት አላላቀቀም።አፍሪቃ የከባቢ ዓየርን የሚበክሉ ኢንዱስትሪዎች ባይኖሯቱም የበለፀጉት ሐገራት የሚያደርሱትን ብክለት መካፈል ግድ ሆኖባታል።ኢትዮጵያን የመሳሰሉ የአፍሪቃ ሐገራት ምጣኔ ሐብታቸዉን ለማሳደግ የሚያደርጉት ጥረት የከበቢ ዓየር ጥበቃን ከግምት ያስገባ መሆኑ አፍሪቃ ለወደፊቱም ከባቢ ዓየርን በካይ እንደማትሆን አመልካች ነዉ ተብሏል።የዛሬዉ ጤናና አካባቢ ዝግጅት የአየር ንብረት ለዉጥንና የአፍሪቃን ጥረት ይቃኛል።

 

ገበያዉ ንጉሴ

አዜብ ታደሰ 

ነጋሽ መሐመድ