1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውደ ዓመት ገበያ  በአዲስ አበባ 

ሐሙስ፣ ጳጉሜን 5 2012

ከከብት ገበያ አንስቶ እስከ ዶሮና ቅመማ ቅመም፤ ከሳር ቄጠማው እስከ ሽንኩርት ድረስ በደራ ገበያ ሲሸጥ ሲሸመት ውሏል።ሸማቾች የከብቶችና የሸቀጦች ዋጋ መናሩን ተናግረዋል።በየገበያው በቂ አቀርቦት መኖሩን ነጋዴዎች ቢናገሩም ገዢዎች ግን በቂ አማራጭ አላገኘነም ነው ያሉት።

https://p.dw.com/p/3iIAh
Addis Abeba I Äthiopischer Neujahrsmarkt
ምስል DW/S. Getu

የአውደ ዓመት ገበያ  በአዲስ አበባ 

የአዲሱ ዓመት አቀባበል ዝግጅት አንዱ አካል የሆነው የዓውደዓመት ገበያ ዛሬም በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች እንደቀድሞው ሲካሄድ መዋሉን የገበያ ስፍራዎችን ተዘዋውሮ የቃኘው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ስዩም ጌቱ ተመልክቷል።አንዳንድ ሸማቾች የከብቶችና የሸቀጦች ዋጋ መናሩን ሲናገሩ ነጋዴዎች ደግሞ ኮሮና ገበያውን አዳክሞታል ብለዋል።በየገበያው በቂ አቀርቦት መኖሩን ነጋዴዎች ቢናገሩም ገዢዎች ግን በቂ አማራጭ አላገኘነም ነው ያሉት።በሾላና በካራ አሎ እንሰሳት ገበያ የተገኘው ስዩም እንደታዘበው ራስን ከኮሮና ተህዋሲ ለመከላከል አብዛኛው ሰው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ቢያደርግም የአካል ርቀትን ጠብቆ ሲገበያይ ግን አልታየም።ነጋዴዎቹና ሸማቾቹ ስለ ዓውደ ዓመት ገበያ የሰጡት አስተያየት እነሆ።
ስዩም ጌቱ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ