1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮጳ ኅብረትና የብሪታንያ የንግድ ውል

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 16 2013

በሕብረቱ መቀመጫ በብራሰልስ የአባል ሃገራቱ ተወካይ አምባሳደሮች ዛሬ በገና በዓል ሕብረቱና ከሕብረቱ አባልነት የወጣችው ብሪታንያ የተስማሙበትን የጋራ የንግድ ውል ለመገምገም ተሰብስበዋል። የዛሬ ሳምንት ሐሙስ ብሪታንያ ጓዟን ጠቅላላ ከአውሮጳ ሕብረት አባልነት ስለምትውጣ ውሉ በፍጥነት እንዲጸድቅ ይፈለጋል።

https://p.dw.com/p/3nDdf
Standbild Dokumentation | KW1 | Brexit Bittersüß
ምስል DW

የአውሮጳ ኅብረትና የብሪታንያ የንግድ ውል

የአውሮጳ ኅብረትና ብሪታንያ ትናንት የንግድ ውል ላይ መድረስ መቻላቸውን የአውሮጳ ሕብረት አባል ሃገራት ደግፈዋል። አባል ሃገራቱ ውሉን በሙሉ ድምጽ ያጸድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከዚያ በፊት በሕብረቱ መቀመጫ በብራሰልስ የአባል ሃገራቱ ተወካይ አምባሳደሮች ዛሬ በገና በዓል ሕብረቱና ከሕብረቱ አባልነት የወጣችው ብሪታንያ የተስማሙበትን የጋራ የንግድ ውል ለመገምገም ተሰብስበዋል። የዛሬ ሳምንት ሐሙስ ብሪታንያ ጓዟን ጠቅላላ ከአውሮጳ ሕብረት አባልነት ስለምትውጣ ውሉ በፍጥነት እንዲጸድቅ ይፈለጋል። ከአንድ ዓመት ድርድር በኋላ ስምምነት ላይ ስለተደረሰበት የብሪታንያና የአውሮጳ ሕብረት የወደ ፊቱ የንግድ ግንኙነት ውል የብራሰልሱ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሤ ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል።
ገበያው ንጉሤ 
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ