1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮጳ ኅብረት በሱዳን እና ሊቢያ ጉዳይ መወያየቱ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 6 2011

የአውሮጳ ሕብረት ውጭ ጉዳይ ሚንሥትሮች ትናንት ቤልጂየም መዲና ብራስልስ ውስጥ ባደረጉት ስብሰባ በዓለም ዙሪያ ለፀጥታ አሳሳቢ ባሏቸው ጉዳዮች ላይ መክረው ውሳኔ አስተላልፈዋል። የሊቢያ እና የሳህል ቃጣና የፀጥታ ኹኔታ በጥልቀት የተመረመረ ሲሆን፤ የሱዳን የፖለቲካ ኹኔታ ግን ብዙም አልተወራለትም።

https://p.dw.com/p/3IUGY
Brüssel Treffen EU-Außenminister Federica Mogherini
ምስል picture-alliance/AA/D. Aydemir

የሊቢያ እና ሱዳን ጉዳይ በአውሮጳ ኅብረት

ሆኖም የሱዳን ወታደራዊ አዛዦች ከቀድሞው ፕሬዚደንት ዖማር ኧል በሽር የወሰዱትን ሥልጣን ወደ ሲቪሉ ማኅበረሰብ ማስረከብ እንደሚገባቸው የያዙት አቋም አኹንም የጸና መኾኑን ሕብረቱ ገልጧል። የገልፍ ተፎካካሪ ሃገራት በሱዳን ውስጣዊ የፖለቲካ ጉዳይ ጣልቃ መግባት ሥልጣኑን ወደ ሲቪሉ ማኅበረሰብ ለማሻገር የተጀመረው ጥረት ላይ መሰናክል  እንዳይፈጥር መስጋታቸው ተገልጧል። የአውሮጳ ሕብረት የውጭ ጉዳዮች ኃላፊ ፌደሪካ ሞጎሮኒን እዛው ብራስልስ ውስጥ ያነጋገራቸው ገበያው ንጉሤ ቀጣዩን ዘገባ አጠናቅሮልናል።  

ገበያው ንጉሤ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ