1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳ ኅብረት ጉባኤ

ዓርብ፣ መጋቢት 14 2010

ትናንት የተጀመረዉ የአዉሮጳ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ በዛሬዉ ዕለት ልዩ ልዩ ዉሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቋል። መሪዎቹ ከተነጋገሩባቸዉ አጀንዳዎች መካከል በአሜሪካ እና የአዉሮጳ ኅብረት የንግድ ግንኙነቶች ላይ የተፈጠረዉ ዉዝግብ እና የብሪታንያ እና የኅብረቱ የብሬግዚት ቀጣይ ድርድር ይዘት እና አቅጣጫን የሚመለከተዉ ይገኙበታል።

https://p.dw.com/p/2us3L
Belgien - EU-Gipfel Angela Merkel
ምስል Getty Images/J. Taylor

ትናንት ተጀምሮ ዛሬ ተጠናቀቀ

በተጨማሪም በቅርቡ በብሪታንያ የሚኖሩ የቀድሞ የሩሲያ ሰላይ እና ልጃቸዉ ላይ በተፈጸመዉ የመግደል ሙከራ ምክንያት ከሞስኮ ጋር የተገባባቸዉ ዉዝግቦች እና ግጭቶች ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ። የጉባኤን የማጠቃለያ መግለጫ የተከታተለዉ የብራስልሱ ዘጋቢያችን ገበያዉ ንጉሤ ዝርዝሩን ልኮልናል።

ገበያዉ ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ