1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳ ኅብረት የ 2018 የመጨረሻ ጉባኤ  

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 5 2011

ከሃሙስ ጀምሮ ሲካሄድ የቆየዉ የአዉሮጳ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ልዩ ልዩ ዉሳኔዎችን በማሳለፍ ዛሬ ተጠናቆአል። በዚህ ዓመትና ከዚያ በፊት ጀምሮ የአዉሮጳ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ዋና አጀንዳ ሆነዉ የቆዩት የፈላስያን ጉዳይና የብሪታንያ እና የአዉሮጳ ኅብረት ፍቺ ፤ የብሪግዚት ዶሲዎች ነበሩ።

https://p.dw.com/p/3A8VI
Belgien | EU-Gipfel in Brüssel
ምስል Reuters/Pool/P. v. d. Wouw

የፈላስያን ጉዳይና የብሪታንያ እና የአዉሮጳ ኅብረት ፍቺ ዶሲዎች የነበሩ

ከሐሙስ ጀምሮ ሲካሄድ የቆየዉ የአዉሮጳ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ልዩ ልዩ ዉሳኔዎችን በማሳለፍ ዛሬ ተጠናቆአል። በዚህ ዓመትና ከዚያ በፊት ጀምሮ የአዉሮጳ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ዋና አጀንዳ ሆነዉ የቆዩት የፈላስያን ጉዳይና የብሪታንያ እና የአዉሮጳ ኅብረት ፍቺ ፤ የብሪግዚት ዶሲዎች የነበሩ ሲሆን በዚህኛዉም ጉባኤ ዋናዎቹ የመነጋገርያ አጀንዳዎች ነበሩ። የኅብረቱ መሪዎች ባለፈዉ ወር በተለይ በብሪግዚት ጉዳይ ላይ ተሰብስበዉ በሁለቱ ወገኖች ተደራዳሪዎች የቀረቡትን የብሪታንያን ከህብረቱ መዉጫ ሰነዶች ተቀብለዉ እና ወስነዉ የተነሱ መሆኑ የታወቀ ሲሆን በአሁኑ ወቅት አጀንዳዉ እንደገና የቀረበዉ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስeር ቴሪዛ ሜይ በዉሉ መክንያት ከፍተኛ ተቃዉሞ ስለገጠማቸዉ እና በፓርላማዉም ለማፀደቅ ስለተሳናቸዉ መሆኑ ታዉቋል።  ቴሪዛ ሜይ ይህን ስምንነት ይዘዉ ወደ ሃገራቸዉ ከሄዱ በኋላ ከስልጣን እንዲወርዱ የሚጠይቀዉን የመተማመኛ ድምፅ ያለፉ ቢሆንም ስምምነቱን ለማፀደቅ የሚስችል እስካሁን አላገኙም።   

 

ገበያዉ ንጉሴ

 

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ