1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 የአዉሮጳ ሕብረትና ኢትዮጵያ 

ዓርብ፣ መጋቢት 3 2013

የሕብረቱ ምክር ቤት ትናንት ባወጣዉ መግለጫ «አጋር» ያላት ኢትዮጵያ በተወሳሰበ ችግር ዉስጥ እንደምትገኝ አስታዉቋልም

https://p.dw.com/p/3qYPf
EU-Ratsgebäude in Brüssel
ምስል DW/B. Riegert

የአዉሮጳ ሕብረት ምክር ቤት መግለጫና ኢትዮጵያ

ሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ዉስጥ የሚደረገዉ ወታደራዊ ግጭት ወደ መላዉ የአፍሪቃ ቀንድ እንዳይዛመት የሚያሰጋ መሆኑን የአዉሮጳ ሕብረት አስታወቀ።የሕብረቱ ምክር ቤት ትናንት ባወጣዉ መግለጫ «አጋር» ያላት ኢትዮጵያ በተወሳሰበ ችግር ዉስጥ እንደምትገኝ አስታዉቋልም።የኢትዮጵያ መንግስት በተለይ በትግራይ ክልል ያለዉን ችግር ለማቃለል የሚያደርገዉን ጥረት አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቋል።ሕብረቱ ለኢትዮጵያ መንግስት የበጀት መደጎሚያ ይሰጠዉ የነበረዉን የገንዘብ ድጋፍ ከዚሕ ቀደም ስለማቋረጡ የትናንቱ መግለጫ የጠቀሰዉ ነገር የለም።

ገበያዉ ንጉሴ 

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ