የአዉሮጳ ሕብረት የበጀት ድጎማ ዕቀባ
ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 8 2013ማስታወቂያ
የአዉሮጳ ሕብረት ለኢትዮጵያ መንግስት በጀት መደጎሚያ ሊሰጠዉ የነበረዉን የ90 ሚሊዮን ዩሮ ርዳታ ለሌላ ጊዜ መግፋቱን ትናንት ዘግበን ነበር።ሕብረቱ ርዳታዉን የያዘዉ በትግራዩ ዉጊያ ሰበብ መሆኑን ገልጧልም።የሕብረቱ ባለስልጣናት ዛሬ በሰጡት ዘርዘር ያለ ማብራራያ የተያዘዉ ርዳታ የኢትዮጵያ ክልልሎችን ለማገናኘት፣ ለጤና እና ለስራ ዕድል መርሐ ግብር መስኮች መንግሥት ለሚመድበዉ በጀት መደጎሚያ የሚዉል ነበር።የሕብረቱ ባለስልጣናት እንዳስታወቁት የተያዘዉ በጀት የሚለቀቀዉ ሕብረቱ ያስቀመጣቸዉ ቅድመ ሁኔታዎችን የኢትዮጵያ መንግስት ሲያሟላ ነዉ።
ገበያዉ ንጉሴ
ነጋሽ መሐመድ
እሸቴ በቀለ