1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳ ሕብረት ስለ ሕዳሴዉ ግድብ ሙሌት

ዓርብ፣ ሐምሌ 2 2013

የአዉሮጳ ሕብረት ባወጣዉ መግለጫ ኢትዮጵያ ግድቡን ለሁለተኛ ጊዜ መሙላትዋን ነቅፏል። ሕብረቱ እንደሚለዉ ኢትዮጵያ ሌሎቹ ሐገራት ሳይስማሙ ግድቡን መሙላት መጀመሯ በድርድሩ ሒደትና ዉጤት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል።

https://p.dw.com/p/3wI0M
Äthiopien Addis Abeba | Report | Grand Ethiopian Renaissance Dam
ምስል DW/N. Desalegen

የሕዳሴዉ ግድብ ሁለተኛ ሙሌትና የአዉሮጳ ሕብረት

የፀጥታዉ ምክር ቤት በሕዳሴዉ ግድብ ሰበብ ሥለተነሳዉ ዉዝግብ ትናንት ከመወያየቱ በፊት በዋዜማዉ ሮብ የአዉሮጳ ሕብረት ባወጣዉ መግለጫ ኢትዮጵያ ግድቡን ለሁለተኛ ጊዜ መሙላትዋን ነቅፏል። ሕብረቱ እንደሚለዉ ኢትዮጵያ ሌሎቹ ሐገራት ሳይስማሙ ግድቡን መሙላት መጀመሯ በድርድሩ ሒደትና ዉጤት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል። ይሁንና አንድ የሕብረቱ ቃል አቀባይ እንዳሉት ሕብረቱ የሶስቱ ሐገራት ልዩነት በአፍሪቃ ሕብረት ሸምጋይነት መፈታት አለበት ብሎ ያምናል። የአዉሮጳ ሕብረት የሶስቱን ሐገራት ድርድር  ይታዘባል። 

ገበያው ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

እሸቴ በቀለ