1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሜርክል በእጩነት የመቅረብ ፍላጎት እና አስተያየት

ዓርብ፣ ኅዳር 16 2009

የጀርመን መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል በሚቀጥለው አውሮጳዊ ዓመት 2017 ዓም በሀገራቸው ለሚካሄደው ምክር ቤታዊ ምርጫ ፓርቲያቸውን የክርስትያን ዴሞክራቶች ህብረት፣ በምህፃሩ «ሴ ዴ ኡ»ን ወክለው ለ4ኛ ጊዜ መወዳደር እንደሚፈልጉ ባለፈው እሁድ በይፋ ማሳወቃቸው ይታወሳል።  

https://p.dw.com/p/2T4q8
Angela Merkel kandidiert erneut
ምስል Getty Images/S. Gallup

የሜርክል በእጩነት የመቅረብ ፍላጎት እና አስተያየት

ይኸው የሜርክል ውሳኔ የሀገሪቱን የፖለቲካ ፓርቲዎችንም ሆነ የሀገሪቱን ዜጎች ብዙም አላስገረመም። ብዙ ጀርመናውያን የሜርክልን ዕጩነት በመደገፍ፣ ከርሳቸው የተሻለ ሌላ አማራጭ እንደሌለ እንደሚሰማቸው አስታውቀዋል። አንዳንዶች ደግሞ «ሴ ዴ ኡ»ን የመሩት የቀድሞው የጀርመን መራሒ መንግሥት ሄልሙት ኮል የገጠማቸውን ዓይነት ሽንፈት እንዳይደርስባቸው ስጋታቸውን ገልጸዋል።  ሜርክል የሚወዳደሩበት የፖለቲካ መስክ በጣም በመከፋፈሉ፣ ከርሳቸው በፊት ለጀርመን አማራጭ፣ በምህፃሩ «አ ኤፍ ዴ» የተባለው የቀኝ አክራሪ ፓርቲ በፌዴራዊው ምክር ቤት፣ «ቡንድስታኽ» ለመጀመሪያ ጊዜ ብሔራዊ ውክልና ሊያገኝ የሚችልበት እድል መኖሩን ታዛቢዎች ይናገራሉ።

ይልማ ኃይለሚካኤል

አርያም ተክሌ

አዜብ ታደሰ