1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአንጋፋው ጋዜጠኛ ነጋሽ መሃመድ ሽልማት

ሰኞ፣ የካቲት 7 2014

የኢትዮጵያ ራድዮ ዓለም አቀፍ የራድዮ ቀንን ትላንት ሲያከብር አንጋፋ ጋዜጠኛና የዶቼ ቬለ DW የአማርኛ ቋንቋ አገልግሎት ምክትል ኃላፊ ነጋሽ መሃመድ የሕይወት ዘመን የራድዮ ጋዜጠኝነት ተሸላሚ ሆኗል። ጋዜጠኛ ነጋሽ መሃመድ ገና በአፍላ ዕድሜው በኢትዮጵያ ራድዮ ተቀጥሮ ከባድ ኃላፊነቶችን ተሸክሞ አገሩን እና ህዝቡን አገልግሏል።

https://p.dw.com/p/470bg
DW-Interview mit Frank-Walter Steinmeier
ምስል DW/R. Oberhammer

«እውቅናው በአስችጋሪ ሁኔታ ለሚሰሩ ጋዜጠኞች ጭምርም ነው» ነጋሽ መሐመድ

የኢትዮጵያ ራድዮ ዓለም አቀፍ የራድዮ ቀንን ትላንት ሲያከብር አንጋፋ ጋዜጠኛና የዶቼ ቬለ DW የአማርኛ ቋንቋ አገልግሎት ምክትል ኃላፊ ነጋሽ መሃመድ የሕይወት ዘመን የራድዮ ጋዜጠኝነት ተሸላሚ ሆኗል።  ከነጋሽ መሃመድ  በተጨማሪ ጋዜጠኞች ሃሊማ ኦስማን፣ አለምነህ ዋሴ፣ ኡመር አሊና የሐረር ራድዮ ጣቢያ የመጀመሪያው የቴክኒክ ባለሙያው ጠሃ ባሻም በተመሳሳይ ተሸልመዋል።

DW Kampagne Faces wicf | Negash Mohammed
ምስል DW


የኢትዮጵያ ራድዮ የዘንድሮውን ዓለም አቀፍ የራድዮ ቀን ለማክበር ሲያስብ በራድዮ ዘርፍ ጉልህ ሚና ያበረከቱ የራድዮ ባለውለታዎችን በመሸለም ለወጣት ጋዜጠኞች ትምህርት በሚያስተላልፍ መልኩ መሆን አለበት ብሎ ወሰነ። ገለልተኛ የዳኞች ኮሚቴም አዋቀረ። አድማጮች ጭምር የተሳተፉበት  ሰባት መስፈርቶችን አውጥቶ ጋዜጠኞችን መዘነ። ከ40 ወደ 20 ከዚያም አራት ጋዝጠኞችን እና አንድ የቴክኒክ ባለሙያን  በሙያቸው ባበረክቱት አስተዋኦ የገንዘብ ሽልማት እና የእውቅና የምስክር ወረቀት ሸለማቸው። ወይዘሮ ነጻነት ፈለቀ የኢትዮጵያ ራድዮ ቻናል ኃላፊና የሽልማት ኮሚቴው ሰብሳቢ ስለመስፈርቶቹ በራድዮ ጋዜጠኝነት ከ25 aአመታት በይ ያገለገለ፣ በመስኩ ያካበተውን ልምድ መጽሃፍ በመጻፍ አልያም ጥናቶች በመስራት ልምዱን ለሌሎች ያካፈለ የሚሉ የሚገኙባቸው 7 መስፈርቶች ነበሩ ይላሉ።

ወይዘሮ ነጻነት ስለአንጋፋው ጋዜጠኛ ነጋሽ መሃመድ የግል ምልከታቸው ከነገሩን ነጋሽ በተለይ የውጭ ዜና አዘጋገቡን፣ በኢትዮጵያ FM ራድዮ ታሪክ የመጀመሪያ አሻራወን ያኖረ ባጠቃላይ በራድዮ ጋዜጠኝነት ጉልህ አሻራወን ያኖረ በማለተ ይገልጹታል።

በኢትዮጵያ የተቀያየሩ መንግሥታት ጋዜጠኝነትን መጠቀሚያ የሚያደርጉበት አጋጣሚ እንዳለ ሁሉ መልካም ጅምሮች ቢኖሩም ለሙያው ክብር የሚመጥን እውቅና ሲሰጡ አልተስተዋለም። ነጋሽም እንዲህ አይነት እውቅና ይሰጠኛል ብሎ አልገመተም ነበር። ግን ሆነ። እንደራሱ አገላለጽ "እኔ ለመሾም ለመሸለም ለመታወቅና ለመደነቅ ብዬ ሰርቸ አላወቅም። የምሰራው ለእርካታና አድማጮች  ይተሣለ ነገር ቢያውቁ የአቅሜን ያህል ለማቅረብ ከሁሉም በላይ ደግሞ ራድዬ እንጀራዮ ነው። እና እውቅናው ለኔ ብቻ ሳይሆን በተለይ ኢትዮጵያ ወስጥ በአስችጋሪ ሁኔታ ለሚሰሩ ጋዜጠኞች ጭምር ነው" ብሏል።

ጋዜጠኛ ነጋሽ መሃመድ ገና በአፍላ ዕድሜው በኢትዮጵያ ራድዮ ተቀጥሮ ከባድ ኃላፊነቶችን ተሸክሞ አገሩን እና ህዝቡን አገልግሏል። ከጣቢያው በተጨማሪ የፋናና የዋልታ ጋዜጠኞችን በዜና እና ወቅታዊ ጉዳዩች ዘገባ አሰልጥኗል። የኢትዮጵያ ራድዮ ወደ ድርጅትነት ሲቀየር አሁን የያዘውን ቅርጽ እንዲይዝ የተቋቋመውን ኮሚቴ በኃላፊነት በመምራት በሙያዊ የበኩሉን አበርክቷል። የጣቢያው የስነምግባር መመሪያ ሲዘጋጅም ተባባሪ አጥኚ ነበር። ራድዮ ፋና ሲቋቋምም አሁን ለደረሰበት እድገት አስተዋጽኦ ካደረጉት መካከል አንዱ ነው። 
ከምንም በላይ ደግሞ በኢትዮጵያ የFM ራድዮ ታሪክ ፈር ቀዳጅ አሻራውን አኑሯል። የFM 97.1 በአገሪቱ ሲቋቋም ከሃሳብ ማፍለቅ ጀምሮ ጥናቱን ሙሉበሙሉ በመሥራት አሁን ላበቡ የFM ራድዮዎች የመሰረት ድንጋይ ያኖረው ነጋሽ መሃመድ ነበረ። 
በDW የእስካሁን ቆይታውም ከተወዳጅ የጋዜጠኝነት ሙያዊ አገልግሎቱ በተጨማሪ የፕሮግራሞች መሻሻል ሲደረግ የፕሮግራሞች ስም ከመሰየም አንስቶ ይዘታቸው ምን መሆን እንዳለበት በማጥናት ተግባራዊ እንዲሆኑ አድርጓል። 
ነጋሽ መሃመድ በተለይ ወቅታዊ ጉዳዮችን እያነፈነፈ መረጃዎችን አሰባስቦና አደራጅቶ በውብና ለጀሮ በሚስማማ አስገምጋሚ ድምጹ ባለመሰልቸት በማቅረብ አሁንም በተወዳጅነቱ አንጋፋ ጋዜጠኛ ሆኖ ዘልቋል። 
ዓለም አቀፍ የራድዮ ቀን በዓለም ለ11ኛ በኢትዮጵያ ለ3ኛ ጊዜ ትላንት ተከብሯል።

DW-Interview mit Frank-Walter Steinmeier
ምስል DW/R. Oberhammer
DW-Interview mit Frank-Walter Steinmeier
ምስል DW/R. Oberhammer
Deutschland äthiopischer Friedensminister Muferihat Kamil Ahmed im Interview mit Negash Mohammed
ምስል DW

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ሽዋዬ ለገሰ