1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አምንስቲ ኢንተርናሽናል ለአን ሳን ሱቺ የሰጠውን ማዕረግ አጥፏል

ረቡዕ፣ ኅዳር 5 2011

አምንስቲ ኢንተርናሽናል ለአሁኗ የማይንማር መሪ አን ሳን ሱቺ ቀደም ሲል ሰጥቶት የነበረውን ሽልማት መንጠቁን ከትላንት በስቲያ ሰኞ አስታውቋል። የአምንስቲ ውሳኔውን ያሳለፈው አን ሳን ሱቺ በሀገራቸው የሚፈጸመውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ችላ ብለዋል በሚል ነው።

https://p.dw.com/p/38Ga2
Myanmar Aung San Suu Kyi
ምስል picture-alliance/AP Photo/G. Amarasinghe

አምንስቲ ኢንተርናሽናል ለአን ሳን ሱቺ የሰጠውን ማዕረግ አጥፏል

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም አምንስቲ ኢንተርናሽናል ለቀድሞዋ የማይንማር የሰብዓዊ መብት እና የዲሞክራሲ አቀንቃኝ ወይዘሮ አን ሳን ሱቺ የሰጠውን ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ኒሻን ወይም ሽልማት ነጥቄያለሁ ብሏል። ድርጅቱ ሽልማቱን የነጠቃቸው በሀገራቸው በሮሂንጂያ ሙስሊሞች ላይ ስለሚፈጸመው እና እየተፈጸመ ስላለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ድምጻቸውን ባለማሰማታቸው መሆኑን አስታውቋል። 

ድርጅቱ ባወጣው መግለጫም ለወይዘሮ አን ሳን ሱቺ ሰጥቶት የነበረውን የነጻነት አምባሳደርነት ከፍተኛ ማዕረግ ሲያጥፍባቸው በከፍተኛ ሀዘን መሆኑን ገልጿል። ምክንያቱን ሲጠቅስ ደግሞ ወይዘሮ ሱቺ በማይናማር ወታደሮች የሚፈጸሙትን ወንጀሎች ችላ በማለታቸው እና ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ላይም ዳተኛ በመሆናቸው ነው ይላል።   

ዝርዝር ዘገባውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ። 

ገበያው ንጉሴ

ተስፋለም ወልደየስ

ነጋሽ መሐመድ