1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአባይ ግድብ ድርድር፤ ሱዳንና ግብፅ

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 5 2012

ኢትዮጵያ በዓባይም ይሁን በሌሎች የወንዙ ገባር ወንዞች ላይ የልማት ፕሮጀክቶችን እንዳታከናውን ፣ መሥራት ካሰበችም ከእኛ ፈቃድ ማግኘት አለባት የሚለው የሱዳንና የግብፅ አቋም ወደ አፍሪካ ሕብረት የመጣው ድርድር በተደጋጋሚ እንዲራዘም ማድረጉን አንድ የግድቡ ተደራዳሪ ገለጹ።

https://p.dw.com/p/3gnq1
Äthiopien Grand-Ethiopian-Renaissance-Talsperre
ምስል AFP/Maxar Tech

«በሱዳን ለሁለተኛ ጊዜ የተራዘመዉ የሕዳሴ ድርድር»

ኢትዮጵያ በዓባይም ይሁን በሌሎች የወንዙ ገባር ወንዞች ላይ የልማት ፕሮጀክቶችን እንዳታከናውን ፣ መሥራት ካሰበችም ከእኛ ፈቃድ ማግኘት አለባት የሚለው የሱዳንና የግብፅ አቋም ወደ አፍሪካ ሕብረት የመጣው ድርድር በተደጋጋሚ እንዲራዘም ማድረጉን አንድ የግድቡ ተደራዳሪ ገለጹ። የውኃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር በሦስቱ ሃገራት መካከል ሊካሔድ የታሰበው እና ዳግም በሱዳን ጥያቄ የተራዘመው ድርድር በመጪው ሰኞ ሊካሔድ እንደሚችል አስታውቋል። ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው የግድቡ ተደራዳሪ እንዳሉት በሱዳን አዲስ አስተዳደር ከመጣ ወዲህ የኻርቱም አያያዝ ከግብፅ አቋም ጋር አንድ ሆኗል ብለዋል። ሰሎሞን ሙጬ ከአዲስ አበባ ዝርዝሩን አጠናቅሯል።

ሰሎሞን ሙጬ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ