1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአስገድዶ መድፈር ወንጀል በኢትዮጵያ

ረቡዕ፣ ጥር 13 2012

ባለፈዉ ሰሞን በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ የሚገኝ የሕክምና ባለሞያ ታማሚዉን ማደንዘዣ ተጠቅሞ በመድፈሩ ትልቅ የመነጋገር ርዕስ ሆኖ መሰንበቱን ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።

https://p.dw.com/p/3WTYX
Indien Protest gegen der Vergewaltigung einer Studentin in New Delhi
ምስል Reuters/A. Fadnavis

በሃገራችን የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ይሸፋፈናል

በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ የሚገኝ የሕክምና ባለሞያ ታማሚዉን ማደንዘዣ ተጠቅሞ በመድፈሩ ትልቅ የመነጋገር ርዕስ ሆኖ መሰንቱን ወኪላችን ዮኃንስ ገብረግዚአብሔር ከዝያዉ ከአዲስ አበባ የላከልን ዘገባ ያመለክታል። ጉዳዩን የያዘዉ ፖሊስ ወንጀለኛዉ በፍርድ ቤት ቀርቦ ቅጣት ማግኘቱን ከመግለፁ በዘለለ ዝርዝር መረጃ ለመስጠት አለመፍቀዱ ተመልክቷል። የሕግ ባለሞያ ሴትች ማኅበር በሀገሪቱ ከሚፈፀሙ የአስገድዶ መድፈር እና የወሲብ ትንኮሳዎች ከዘጠኛ በመቶ በላይ ይፋ እንደማይነገሩ ወይም ሕግ ፊት እንደማይቀርቡ ገልጿል። አንድ የፆታ ነክ ጉዳዮች አማካሪ በበኩላቸዉ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የተፈፀመባቸዉ ሴቶች በአስቸኳይ ወደ ጤና ጣብያ ማለትም ሕክምና እንዲሄዱ መክረዋል።

ዮሃንስ ገብረግዚአብሔር

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ