1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ትዕዛዝት

ዓርብ፣ ኅዳር 17 2014

የጦር ሜዳ ውሎዎችን እና ውጤቶችን በተመለከተ ሥልጣን ከተሰጠው አካል ውጪ በየትኛውም የመገናኛ አውታር መግለጫዎችን መስጠትና ማሰራጨትም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዙ ተከልክሏል።ዕዙ የሀሳብ ነፃነትን ሰበብ በማድረግ ልዩ ልዩ የሚዲያ አውታሮችን በመጠቀም በህልውና ዘመቻው ላይ እንቅፋት የሚፈጥሩ ያላቸው አካላትም ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም አስጠንቅቋል።

https://p.dw.com/p/43Xx3
Äthiopien Kebede Desisa
ምስል Seyoum Getu/DW

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ትዕዛዝት

 

የፀጥታ አስከባሪ አካል ሳይሆኑ የፀጥታ አካላትን የደንብ ልብሶች ለብሰው የሚገኙ እና የሽግግር መንግሥት እንመሰርታለን በሚል የሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ የፀጥታ አካላት ሕጋዊ እርምጃ እንዲወስዱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ትናንት ትዕዛዝ አስተላልፏል። ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን ፣ የጦር ሜዳ ውሎዎችን እና ውጤቶችን በተመለከተ ሥልጣን ከተሰጠው አካል ውጪ በየትኛውም የመገናኛ አውታር መግለጫዎችን መስጠትና ማሰራጨትም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዙ ተከልክሏል።ዕዙ የሀሳብ ነፃነትን ሰበብ በማድረግ ልዩ ልዩ የሚዲያ አውታሮችን በመጠቀም የሽብር ቡድኑን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ በመደገፍ በህልውና ዘመቻው ላይ እንቅፋት የሚፈጥሩ ያላቸው አካላትም ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም አስጠንቅቋል።

ሰሎሞን ሙጬ

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሰ