1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአርብ ታኅሣሥ 10 ቀን፣ 2012 ዓ.ም የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 10 2012

የአቶ ኃ/ማርያም ሹመት በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ከእንኳን ደስ አለዎ መልዕክቶች አንስቶ እስከ ጠንካራ ትችቶችና ወቀሳዎች አስተናግዷል። ዳዊት ያደታ ወደላይ እንዲወጡ እንገፋቸዋለን እንጂ አንጎትታቸዉም።በማለት ድጋፋቸውን ገልጸውላቸዋል።ተስፋሁን በልሁ ደግሞ «የሀገሩን ግጭት ያልፈታ አሁን የዓለምን ግጭት ይፈታል ብለው ይሾማሉ ሲሉ ጠይቀዋል»

https://p.dw.com/p/3VA7W
Hailemariam Desalegn, ehemaliger äthiopischer Ministerpräsident
ምስል DW

የአርብ ታኅሣሥ 10 ቀን፣ 2012 ዓ.ም የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት


የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ International Crisis Group በእንግሊዘኛ ምህጻሩ ICG የተሰኘዉ ዓለም አቀፍ የግጭቶች አጥኚ ተቋም የባላአደራዎች ቦርድ አባል ሆነዉ መሾም ከሰሞኑ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች መነጋገሪያ ርዕሶች አንዱ ነበር።የኃይለ ማርያም ሹመት በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ከእንኳን ደስ አለዎ መልዕክቶች አንስቶ እስከ ጠንካራ ትችቶችና ወቀሳዎችን አስተናግዷል።አቡ አሚን ያሲን በአጭሩ «ኢትዮጵያ ከፍ እያለች ነው በአለም አሬና መልካም ሥራ ኃይሌ ሲሉ መልካም ምኞታቸውን ገልጸውላቸዋል።ማሂ ነኝ እናቴን ናፋቂ በሚል የፌስቡክ ስም እወነት እና ንጋት እያደረ ይጠራል ኃይለ ማርያም ለሚዲያ ከፍሎ ፕሮፖጋንዳ አያስወራም በቃ የስራ ሰው ክብሩ የሀገር ነው ብለዋል።ፈየራ አበራ፣ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በ6 ዓመት የሥልጣን ዘመናቸው ያደረጉት ጥሩ ነገር ቢኖር ከሥልጣን መውረዳቸው ነው»ሲሉ፤ሳሙኤል ታከለ ቢግሳ ደግሞ «ኢትዮጽያን እዚህ ውጥንቅጥ ውስጥ የከተታት ሰው የግጭት አጥኝ ሆኖ ሲመረጥ ካሉ በኋላ «እውነትም ዓለም ፍትሀዊ ናት» ሲሉ አስተያየታቸውን በስላቅ ደምድሟል። ሃብታሙ ፈንታሁን ግንበኞች የናቁት ድንጋይ  የማዕዘን እራስ ሆነ ብራቮ ደሱ! ሲሉ አወድሰዋቸዋል።መስፍን ዋልተሮም በተመሳሳይ ግንበኞች የናቁት የማዕዘን ራስ ሆነ ይገባዋታል ከብቃትዎም በላይ ነው በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። አቶ ኃይለማርያምን ኃይልሾ በማለት አስተያየታቸውን የሚጀምሩት ማክቤል አበበ «እንኳን ደስ አለን ኢትዮጵያኖች በዓለም ህዝብ ፊት ክብርና ዝና የማግኘት ውጤት በጎ በማሰብ በበጎ ስራዎችን የመሥራት ውጤት ነው።ይሉና እግዝአብሔር ከፍ ከፍ ያደረገውን ሊቃወም የሚችል አንዳች ሰው የለምና ብለዋል። ዳዊት ያደታ ደግሞ «የተከበሩ የኢፊድሪ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የተሳካ የስራ ጊዜ ስመኝልዎት ለአርአያነት የሚበቃ መልካም ስራ እንደሚሰሩ በመተማመን ነዉ። ኢትዮጵያዉያንን በአለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ በከፍተኛ የስራ ሐላፊነት ላይ ማየት ደስ ይላል። በምንችለዉ አቅም ወደላይ እንዲወጡ እንገፋቸዋለን እንጂ አንጎትታቸዉም።በማለት ድጋፋቸውን ገልጸውላቸዋል። ከአቶ ኃይለ ማርያም በተጨማሪ የቀድሞ የአውሮጳ ህብረት የውጭ ጉዳዮች ሃላፊ ፌደሪካ ሞጎሮኒም ተመሳሳይ ሹመት አግኝተዋል።የግጭት መንስኤዎችንና መከላከያዎችን በማጥናት መፍትሄያቸውንም የሚጠቁመው ክራይስስ ግሩፕ ሁለቱን ፖለቲከኞች ለባለአደራ ቦርድ አባልነት የሾመው በዳበረ የፖለቲካ ልምዳቸው መሆኑን አስታውቋል። 
አበበ ገደፋው ስለ ሹመቱ በሰጡት አስተያየት« ትክክል ነው ሲያጋጭ የነበረ ሰው የግጭቱን ምክንያት አያውቅም አይባልም በተለይ ለኢትዮጵያ ጥሩ ከሰራበት፤የሚል አስተያየት ሰጥተዋል።ተስፋሁን በልሁ «የሀገሩን ግጭት ያልፈታ አሁን የዓለምን ግጭት ይፈታል ብለው ይሾማሉ ነገ ደግሞ አንድ ነገር ቢፈጠር እነሱ የነገሩኝን ነው የምወስነው እንዳይለን።»ሲሉ አልፎሄያጅ ላይኔ በሚል የፌስ ቡክ ስም «ያገሩን ግጭት መፍታት አቅቶት ከስልጣን እንደወረደ አልሰሙም ማለት ነው?ወይስ በግጭቱ እንዲሳተፍ ነው?የሚል ጥያቄ አቅርበዋል። የኢትዮጵያን ግጭት የአወጋገድ ብልሃት ሳይነግሩን! የዓለም ?ጉድ በል ጎንደር ነው ነገርየው!ይላል የማናስቦ በርሄ አስተያየት።ሰሎሞን አበራ «ይገባሃል የእኛ ጀግና !! የለውጡ ምርጥ ሞተር በዝምታ ብዙ እንደሚሰራ አስተምረኽናል!!ሲሉ አሞግሰዋቸዋል።
አያሌው አስረስ ደግሞ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።«እጅግ ደስ የሚልና ስምን ከፍ አድርጎ የሚያሥጠራ ሥራ የሚሠሩበት ይሆን ዘንድ ከልብ እመኛለሁ በማለት። 
ባለፈዉ ዓመቱ የሰኔ 15ቱ  የአማራ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናትን ግድያ ተጠርጥረው የተከሰሱ የክልሉ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ከትናንት በስተያ በነፃ መሰናበት በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አስተያየት ከተሰጠባቸው ጉዳዮች መካከል ይገኝበታል።ባሕርዳር ያስቻለዉ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀድሞዎቹ የአማራ ክልል ከፍተኛ የፀጥታ  ባለስልጣናት ብርጌድየር ጄኔራል ተፈራ ማሞ፣ኮሎኔል አለበል አማረ፤ኮሎኔል በአምላክ ተስፋና ኮማንደር ጌትነት ሺፈራዉን ነው በነፃ ያሰናበተው።ታስረው የነበሩት ተጠርጣሪዎቹ  ባለፈው ጥቅምት በገንዘብ ዋስትና ተለቀው ነበር። በዋስ ከተፈቱ በኋላም ሲከራከሩ በነበሩት በነዚሁ ተከሳሾች ላይ የተመሰረተዉን ክስ የሚያጠናክር የሰዉም ሆነ የቴክኒክ ማስረጃ ባለመገኘቱ ፍርድ ቤቱ አራቱንም በነፃ አሰናብቷል።  ደስ ይላል በጣም ብለዋል ካሳሁን ጎሽየ ዛያዘው በፌስቡክ ባሰፈሩት አስተያየት።እንኳን በሰላም ወጡ ያሉት ደግሞ ጉዋጉ ለገሰ ናቸው። ድሮስ ያለወንጀላቸው የወንጀል ድራማ ሰርተው አስረው የህዝብ ልጅ ያሰቃያሉ። ያሉት በሕግ አምላክ እነ ክርስቲያን ታደለም ይፈቱ ሲሉ ተማጽነዋል ጌታቸው አበራ በፌስቡክ ። "ፍርድ ቤታችን ነፃና ፍትሃዊ  መሆኑ ነው ሲሉ ሲሉ የገለጹት ደግሞ እስከዳር አስፋው ናቸው።ሰላም ግዛ ደግሞ ጥያቄ አቅርበዋል ወደ ሥራ ገበታቸው ባስቸኳይ እንዲመለሱ እና  ተገቢውም ካሳ እንዲከፈላቸው ፤ የተንገላቱት በተበላሸ አሰራር ስለሆነ ሃላፊነት ያለባቸው ሰዎች በህግ ይጠየቁም ብለዋል።ብሥራት መለሰ ገበየውም ተመሳሳይ ጥያቄ አቅርበዋል።«ወይሠው ያለሥራቸው እሥካሁንም መሠቃያቸው.ያለአግባብ ነው ወደሥራ.ገበታቸው ይመለሡ ሲሉ ይስማሸዋ ዘግዮንም ባስቸኳይ ወደ ስራቸው ሊመለሱ ይገባል!በማለት ጠይቀዋል።ሃሰን አብዲ ሀሰን ደግሞ ምሥጋና አቅርበዋል።ለበጎ ነው የአማራ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እናመሰግናለን!!በማለት።ከናንተ በፊት ነጻ መሆናቸው ያኔ የታሰሩ እለት ህዝብ ያውቃል። በመጀመሪያም መታሰር አልነበረባቸውም ይላል የፀጋዬ ታደሰ ናቸው። 
በኢትዮጵያ ለ10ኛ ክፍል ተማሪዎች ይሰጥ የነበረው የአጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ፈተና ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ መቅረቱን የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ዳግም ካረጋገጠ በኋላ በማህበራዊ መገናና ዘዴዎች የተለያዩ አስተያየቶች ተስተናግደዋል። የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገብረ እግዚአብሔር ለዶቼ ቬለ DW እንደተናገሩት ይህ የተወሰነው አዲስ በተዘጋጀው የትምህርት ፍኖተ ካርታ ላይ በቀረበው ሃሳብ መሠረት ነው። ሃላፊው የስምንተኛ ክፍል አጠቃላይ ፈተና እንደሚኖርም ተናግረዋል። 
ራስ ቦርጋ ጥሩ ሲሰራ ማመስገን አስፈላጊነው እስከ 12 መሆኑ ደስ ብሎኛል፡፡ሲሉ ዋሲነት ነጋሽ ደግሞ የፍኖተ ካርታው ማስፈፀሚያ መመሪያ የሚወጣው 2013 ዓ.ም ስራው የሚሰራው 2012 ዓ.ም ስለዚህ መመሪያ ደንቡ በቶሎ ይምጣልን።ሌላው ደግሞ 6ኛ እና 8ኛ ክፍል ላይ ቅድመ ዝግጅት ቢደረግ በማለት ጠቁመዋል።ሄኖክ ፋሲል እንዲህ ነው ለትውልድ ማሰብ በርቱ ከጎናችሁ ነንሲሉ ድጋፋቸውን አስፍረዋል።ሰሎሞን ይልማ እሸቱ ኪሳራ ነበር እንኳን ቀረ ሁሉም እስከ 12 ይማር ሲል እኔ ነኝ በሚል የፌስቡክ ስም አስተያየታቸውን የሰጡ ደግሞ« በዚሁ የመምሕር ክብር የደሞዝ የበላይነት ቢታሰብበት ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም ይደርስ ነበር ሲሉ አሳስበዋል።በጣም ደስ የሚል ዜና ነው ፤ አሁን ገና ትውልድ ዳነ።ያሉት ደግሞ ባርኮት አሰፋ ናቸው።ሙሉ ብርሃኔ ደግሞ እንኳን ቀረ ጥሩ ነው ለፈታኞች እየተባለ የህዝብ ገንዘብ ሲባክን ነበር በማለት የ10ኛ ክፍል ፈተና መቅረት ገንዘብ የገንዘብ ብክነትንም እንደሚያስቀር ጠቁመዋል።መስፍን ግርማ «በቀስታ ግን በእርግጠኝነት ለውጥ እየመጣ ነው» የሚለው ደግሞ የመስፍን ግርማ አስተያየት ነው።
በኢትዮጵያ ላለፉት 18 አመታት ይሰጥ የነበረው የ10ኛ ክፍል ፈተና መቅረቱን ከዚህ ቀደም የትምህርት ሚኒስትሩም ተናግረው ነበር። የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተርባለፈው ማክሰኞ ጉዳዩ እንደገና የተነሳው በተለያዩ ምክንያቶች የመረጃ ክፍተት በተፈጠረባቸው አንዳንድ ቦታዎች የፈተና ዝግጅትን አስመልክቶ ጥያቄዎች በመነሳታቸው መሆኑን ለዶቼቬለ ተናግረዋል።

Äthiopien Addis Abeba Beschwerden über Abiturprüfung
ምስል DW/Solomon Muchie
Äthiopien Gerichtshof in Bahir Dar
ምስል DW/A. Mekonnen

ኂሩት መለሰ

እሸቴ በቀለ