1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአርበኞች ግንቦት 7 ባለሥልጣን መልቀቅያ

ማክሰኞ፣ መጋቢት 10 2011

አቶ ነዓምን ንቅናቄዉን ጥለዉ ለመዉጣት የወሰኑበት ምክንያትም የኢትዮጵያ መንግስት ወደ ከኤርትራ በረኃ ወደ ኢትዮጵያ ትጥቃቸዉን ፈተዉ የገቡት የንቅናቄዉን የቀድሞ ታጋዮች ለማሰልጠንና ዳግም ከሕብረቱሰቡ እንዲቀየጡ ለማድረግ የገባዉን ቃል ገቢር ባለማድረጉ ነዉ። የቀድሞዎቹ ታጋዮች ችግር ለ«ሕሊና እረፍት የሚነሳ» ብለዉታል።

https://p.dw.com/p/3FJf4
Neamin Zeleke
ምስል privat

የቀድሞዎቹ ታጋዮች ችግር ለ«ሕሊና እረፍት የሚነሳ ነዉ

የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እና የዉጪ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ነዓምን ዘለቀ እራሳቸዉን ከንቅናቄዉ አባልነት ማግለላቸዉን አረጋገጡ። አቶ ነዓምን ሥልጣን መልቀቃቸዉ በያዝነዉ ሳምንት ሰኞ ከቀትር በኋላ በማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ተዘግቦ ነበር። አቶ ነዓምን ንቅናቄዉን ጥለዉ ለመዉጣት የወሰኑበት ምክንያትም የኢትዮጵያ መንግስት ከኤርትራ በረኃ ወደ ኢትዮጵያ ትጥቃቸዉን ፈተዉ የገቡት የንቅናቄዉን የቀድሞ ታጋዮችን ለማሰልጠንና ዳግም ከሕብረቱሰቡ እንዲቀየጡ ለማድረግ የገባዉን ቃል ገቢር ባለማድረጉ ነዉ ሲሉ ዛሬ ለ «DW» በሰጡት ቃለ መጠይቅ ተናግረዋል። አቶ ነዓምን እንደሚሉት  የንቅናቄዉን የቀስሞ ታጋዮች መልሶ ለማቋቋም መንግስት የገባዉን ቃል እንዲያከብር እሳቸዉን ጨምሮ የንቅናቄዉ ባለሥልጣናት ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርጉም ዉጤት አላገኙም። የቀድሞዎቹ ታጋዮችን ችግር ለ«ሕሊና እረፍት የሚነሳ ብለዉታል። በአሁኑ ወቅት በሰሜን አሜሪካ የሚገኙትን አቶ ነዓምን ዘለቀ ከ «DW» ጋር አጠር ያለ ቃለ ምልልስ አድርገዋል።

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ