1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአምስት ኦሮሞ ድርጅቶች የጋራ መግለጫ 

ማክሰኞ፣ መስከረም 15 2011

የኦሮሞ ሕዝብ አንድነት አንገብጋቢ የወቅቱን የፖለቲካ አስመልክቶ አምስት የኦሮሞ ድርጅቶች የጋራ መግለጫ አወጡ። በመግለጫቸዉ የኦሮሞ ማንነትን ለማጥፋት እየተደረገ ያለዉን ሙከራ፤ ፊንፊኔን በተመለከተ የሚሉ ጉዳዮች ይገኙበታል።

https://p.dw.com/p/35U0x
Flash-Galerie Der Blick aus meinem Fenster Addis Abeba Äthiopien
ምስል S. Mengist

የኦሮሞ እና የአማራ ሕዝብ ጨቋኝ አገዛዞችን ለማስወገድ ታግለዋል

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር፤ የኦሮሞ ፌደራል ኮንግረስ ፤ የተባበሩት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር፤ የኦሮሚያ ነጻነት አንድነት ግንባር እና የኦሮሞ ዶሞክራሲ ግንባር በኦሮሞ እሴቶችና ጥቅም ላይ በመመርኮዝ የኦሮሞን አንድነት በሚያንፀባርቁ እና አንድ በሚያደርጉዋቸዉ እንዲሁም በወቅታዊ አንገብጋቢ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግለጫ ማዉጣታቸዉን ገልፀዋል። መግለጫዉን በተመለከተ አጠር ያለ ማብራርያ የሰጡን የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ ናቸዉ።


አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ