1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን

ዓርብ፣ ግንቦት 20 2013

«ከአሜሪካ ጋር ከመፎካከር የሚያዋጣንን መንገድ መፈለጉ ይሻላል። ኢትዮጵያ አሜሪካን ላይ መአቀብ የመጣል አቅሙ የላትም። ነገሩን ሰፋ አድርገን ከአገር ጥቅም አንፃር አይተን ሳንሸነፍ ተሸንፈን ሳናሸንፍ አሸንፈን አገርን ከመከፋፈል ፣ከኑሮ ውድነት እና እርስ በርሰ ጦርነት ማዳን አለብን።»

https://p.dw.com/p/3u7Xa
US-Außenminister Blinken in Island
ምስል Saul Loeb/AFP/AP/dpa/picture alliance

ማዕቀቡ በርካቶችን አስቆጥቷል

ዩናይትድ ስቴትስ ባለፉት ስድስት ወራት በትግራይ የተካሄደውን ውጊያ በማባባስ ተጠያቂ ባላቻቸው  በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ባለሥልጣናት ላይ ፣የመግቢያ ፈቃድ(ቪዛ) እገዳና የኤኮኖሚ እንዲሁም የደኅንነት ድጋፍ ማዕቀብ  መጣሏን  የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ አንቶኒ ብሊንከን ግንቦት 15 ቀን 2013 ዓም ባወጡት መግለጫ ነበር ያሳወቁት። ብሊንከን በመግለጫቸው የጉዞ እገዳው «የአሁን ወይም የቀድሞ የኢትዮጵያ ወይም የኤርትራ መንግሥት ባለሥልጣናትን፣ የአማራ ክልልና መደበኛ ያልሆኑ ኃይላትን እንዲሁም የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ «ሕወሓት» አባላትን ጨምሮ ሌሎች ግለሰቦችንና ቤተሰቦቻቸውን  እንደሚያካትት» ገልጸዋል።«ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያ በምትሰጠው የኤኮኖሚና የደኅንነት ድጋፎች ላይ መጠነ ሰፊ ገደብ መጣሏንም አስታውቀዋል። ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ መጣሏ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በርካታ ተቃውሞዎች ተሰንዝረውበታል።የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በማግስቱ በፌስቡክ ገጹ ለብሊንከን መግለጫ በሰጠው መልስ    ፣ ማዕቀቡን «የሁለቱን ሃገራት የረዥም ዘመን ጠቃሚ ግንኙነት በእጅጉ የሚጎዳና በጣም አሳዛኝ ሲል ተቃውሞ ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባቷን ከቀጠለች ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጤን እንደምትገደድ አስጠንቅቋል።«በጣም አሳዛኙ ነገር ከሁለት ሳምንት በፊት አሸባሪ ተብሎ ከተፈረጀው ከህወሓት ጋር መንግሥት እኩል ተቀምጦ እንዲደራደር ለማስገደድ መሞከር መሆኑን» የጠቀሰው  መግለጫ ሙከራው  የአስተዳደሩን አሳሳች አቀራረብ የሚያስረዳ አሸባሪ የተባለው ቡድን እንዲያንሰራራ የማድረግ «አፍራሽና ተግባራዊ መሆን የማይችል ሙከራ ሲልም አጣጥሏል።በርካታ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ተጠቃሚዎች በጉዳዩ ላይ ቁጣ ትችት ማሳሰቢያና ማስጠንቀቂያ የያዙ አስተያየቶችን በአንድ ወገን ሲሰነዝሩ በሌላ ወገን ደግሞ ሰከን እንበል ስሜታዊ አንሁን ጥቅምና ጉዳቱን እናጢን ሲሉ ህዝብንም መንግሥትንም ያሳሰቡም ጥቂት አይደሉም።

Äthiopien Logo des Außenministeriums

ዓለማየሁ ዞስትየት በሚል የፌስስቡክ ስም የሰፈረው አስተያየት  

«ኢትዮጵያ የትግራይ ጉዳይ እንዳይፈታ አደናቅፋለች ማለት ትግራይ ዉስጥ ያለው ጉዳይ የኢትዮጵያ ጉዳይ አይደለም ወይም ትግራይን እንደሌላ አካል አደረጎ እኔ ልፍታልህ ኤኔ የሚልህን አደርግ የሚል የኢትዮጵያ ሉአላዊ ሀገርነት የሚንድ የባርነት አስተሳሰብ ነዉ።የ አሜሪካ መንግስት በሰብዓዊ መብት ጥሰት ስም የራሳቸውን ፍላጎት ለመጫን የተደረገ ጫና ነዉ።ይላል

አሜሪካ እውነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ የቆመች አይደለችም በማለት ሃሳባቸውን የጀመሩት ወንድሙ ፉፋ

ለዚህ መሳያው ኢትዮጵያ ለ27ዓመት የተደረጉትን (5)የፌክ የሀሰት ማለታቸው ነው ምርጫዎችን ግልፅና ተአማኒ ምርጫ ስትል የሀገሬን የህዝብ ድምፅ በዶላር ገስታለች አሜሪካ እውነት ለኢትዮጵያውያን ፍትህና ዲሞክራሲ የቆመች ብትሆን ህውሓት በህዝብና በራሱውስጥ ባለው ግፊት ከ4ኪሎ ሸሽቶመቀሌ ከከተመ በኋላ በእብሪት የጦርነት ከበሮ ሲደልቅ የነበረው ማነው? የሀገር መከላከያላይ በለሊት ጥቃት ያደረሰው ማነው በማይካድራ ለፍቶአዳሪ ወንድሞቻችንን የጨፈጨፈና ያስጨፈጨፈ ማነው?ሮኬቶችን ሀገርውሰረጥ ጎንደርና ባህርዳር ላይ ከሀገርውጭ በጎረቤታችን ኤርትሪያ አስመራላይ ካንድም ሁለትሦስቴ ማን ሮኬት ተኮሰ»በማለት ከጠየቁ በኋላ ለኢትዮጵያውያንም ዋናው ነገር ተግቶ ሰርቶ ከችግር መውጣት ሲሆን እስከዛው ግን አማራጮቻችንን በጥንቃቄ እንጠቀም በማለት መክረዋል።

ናቡቴ በሚል የፌስቡክ ስም የተሰጠ አስተያየት የቪዛ ክልከላው/እቀባው የሚጎዳው ነገር የለም! የኢኮኖሚ ማዕቀቡ ጊዚያዊ ጉዳት ይኖረዋል! እንደሚታወቀው የሃገራችን የኢኮኖሚ ሁኔታ ችግር ውስጥ ወድቋል! ከውጭ በርዳታ ስም የሚመጡ ዶላሮች ናቸው የሃገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ፍጆታ የሚሸፍኑት! የውጭ ንግዳችን ከዚህ ግባ የሚባል አይደለም!  ስለዚህ ኢትዮጵያ የራሷን ክብር ማስጥበቅ አለባት! ኢትዮጵያ ክብርት ሃገር ናትና ለአሜሪካ ማዕቀብ ምላሽ ልትሰጥ ግድ ይላታል! የራሷን የችግር ጊዜ እቅድ ማውጣት አለባት! ከምዕራባዊያን በተቃራኒ ከቆሙ ሃገራት ጋር ኢኮኖሚዋን ማስተሳሰር አለባት!የሚሉትን አማራጮችንም ጠቁመዋል።

ከፍያለው ነጋሳ ቴሶ ደግሞ ስጋት አላቸው፤ ጉዳዩን በጥንቃቄ እናጢን ይላሉ  ።

Tigray-Konflikt | Äthiopien PK Regierungssprecher Dina Mufti
ምስል Solomon Muchie/DW

«ኢትዮጵያ ከዩናይትድ እስቴትስ ጋር ግብግብ ውስጥ መግባቷን ትታ አለመግባባቶችን በድፕሎማሲያዊ መንገድ ካልፈታች ያለምንም ጥርጥር የሀገሪቱ ኢኮኖሚ እንደሚሽመደመድ ከዚህም የተነሳ ህዝቡ ክፉኛ ልጎዳ እንደሚችል ለመተንበይ ነብይ መሆን አያስፈልግም። ወደ ምሥራቅ ማዘንበል የሚባለው ነገር በአንድ እጅ ማጨብጨብ ነዉ የሚሆነዉ፤ የትም አያደርስም። ስለዚህ በስሜት መንዳቱን ትተን በስልታዊ ትንተና ነገሮችን ብናጤን ጠቃሚ ይመስለኛል።»በማለት ከፍያለው ሃሳባቸውን አጠቃለዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ የተቃዋሙት ኢትዮጵያውያን ብቻ አይደሉም።  ታዋቂው የዩናይትድ ስቴትስ ሴናተር ሪፐብሊካኑ ጂም ኢንሆፍም ኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ  መጣሉን ተቃውመዋል።ኢንሆፍ በትዊተር የባይደንን ጠንካራ የቪዛ ማዕቀብ እንደሚቃወሙ ገልጸው እርምጃው ወደ ሰላማዊ መፍትሄ ለመጠጋት አይበጅም ሲሉም ነቅፈዋል።ግጭቶችን ለማስቆም ለምትሰራው ለኢትዮጵያ የኛ ድጋፍ ነው የሚያስፈልጋት ብለዋልም

ሀብተ ቶማስ በፌስቡክ ለአሜሪካን አጭር መልዕክት አስተላልፈዋል«እጃችሁን ከኢትዮጵያ ላይ አንሱ  መጀመሪያ የጥቁር አሜሪካውያንን ችግር አቃሉ» የሚል

አሁን ኢትዮጵያን የሚመራው መንግሥት በአሜሪካ ላይ ምንም ዓይነት ተጽእኖ ሊያደርግ አይችልም።ጥርስ የሌለው አንበሳ ነው የሚለው ምህረተ አብ ገብረስላሴ በሚል ስም በፌስቡክ የሰፈረ መልዕክት ነው።

አባላቱ የቪዛ ማዕቀብ የተጣለባቸው፣በኢትዮጵያ መንግሥት በአሸባሪነት  የተፈረጀው የቀድሞ የትግራይ ክልል ገዥ ፓርቲ ህወሓት ባወጣው መግለጫ «የኢሳያስ አፈወርቂና የዐቢይ አህመድ አገዛዝ» ሲል በጠቀሳቸው በኢትዮጵያና በኤርትራ ላይ የባይደን አስተዳደር የወሰደውን እርምጃ «ወቅታዊ ተገቢ እና አስፈላጊ »ሲል አወድሶ፤ሆኖም የቪዛ እገዳው የህወሓት አባላትን መጨመሩ ግራ እንዳጋባው በፌስቡክ ባሰራጨው መግለጫ አስታውቋል። በህዝብም ሆነ በተቋም ላይ ወንጀል አልፈጸምኩም ፣ እንደ ትግራይ ህዝብ ተበዳይ ነኝ ያለው ህወሓት የባይደን አስተዳደር በአባላቱ ላይ የጣለውን የቪዛ እገዳ ውሳኔውን ዳግም እንዲመረምርና እንዲያጤን ጥሪ አቅርቧል።

አንቶኒ ብሊንከን በእሁዱ መግለጫቸው« ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ቢደረጉም በውጊያው የሚካፈሉ ወገኖች የትግራዩን ግጭት ለማስቆምም ሆነ ለፖለቲካዊ ቀውሱ ሰላማዊ መፍትሄ ለመፈለግ ምንም ዓይነት ትርጉም ያለው እርምጃ አልወሰዱም »ሲሉ ወቅሰው ነበር ።

መሀመድ አሚን ደግሞ

«ከአሜሪካ ጋር ከመፎካከር የሚያዋጣንን መንገድ መፈለጉ ይሻላል። ኢትዮጵያ አሜሪካን ላይ መአቀብ መጣል አቅሙ የላትም። ነገሩን ሰፋ አድርገን ከአገር ጥቅም አንፃር አይተን ሳንሸነፍ ተሸንፈን ሳናሸንፍ አሸንፈን አገርን ከመከፋፈልከኑሮ ውድነት እና ከእርስ በርሰ ጦርነት ማዳን አለብን።ሲሉም መክረዋል።

በኢኮኖሚ እጎዳለው ካሉ ጠላትነታቸው ኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ነው ባለስልጣናት ላይደለም ምክንያቱም ህዝብን ከችግር የሚያወጡ ስራዎች ህዝቡ እየሰራ እራሱን እንዳይች ከምቀኝነት የመነጨ ነው ትግራ ያለው ሁኔታ አሳስቦቸው አይደለም በውስጥ ጉዳያችን እንደመግቢያ ምክኔያት የተጠቀሙት ያሉት ኤም ዲ ነኝ ያሉ የፌስቡክ ተጠቃሚ ናቸው።

በአሜሪካ መንግስት ላይ ተመሣሣይ ማዕቀብ ለመጣል መሞከር ብዙም አዋጭ አካሄድ አይሆንም። ከዚህ የተሻለ እርምጃ ሊሆን የሚችለው "አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የጣለችው ማዕቀብ ታማኝ የሆነ መረጃ ላይ የተመሠረተ ባለመሆኑ ትክክለኛ መረጃ ሲደርሳት በውሳኔዋ እነደምትፀፀት እና ወደ ቀድሞውና ጠንካራው ግንኙነታችን እንደምንመለስ ተስፋ አለን በኢትዮጵያ በኩል አሁንም ከአሜሪካ ጋር በሚያስማሙን ጉዳዮች ላይ መልካም ግንኙነታችን ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ለማሣወቅ እንወዳለን " የሚል መግለጫ በማውጣት ነገሩን ማቅለል ይሻላል ባይ ነኝ ።ካልሆነ ግን ለጠላቶቻችን ደስታ መፍጠር ነው የሚሆነው  እውነቱ ይነገር በሚል ስም በፌስቡክ የሰፈረ አስተያየት ነው።

ኂሩት መለሰ