የአሜሪካ ባለሥልጣናት ተደጋጋሚ የኢትዮጵያ ጉብኝት
ዓርብ፣ ነሐሴ 7 2013ማስታወቂያ
የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ምልዕክተኛ በሦስት ወራት ልዩነት ውስጥ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚሄዱ ይጠበቃል። ከመደበኛው የውጭ ጉዳይ እና የኤምባሲ አካሄድ በዘለለ በአሜሪካ የውጭ ግንኙነት አሠራር ልዩ መልዕክተኛ ወደ አንድ አገር ሲላክ በአገሪቱ ፕሬዝዳንት ለጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት መሰጠቱን ማሳያ መሆኑን አንድ የፖለቲካ ሳይንስ ዐዋቂ ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል። እንደእሳቸው በሌላ በኩል ደግሞ አሜሪካ ጉዳዩን ወደ ድርድር የመውሰድ ፍላጎቷ ላለመሳካቱ ማሳያ ሊሆንም ይችላል። የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የብሔራዊ ፀጥታ አማካሪ የልዩ መልዕክተኛውን ጉብኝት አስመልክቶ በማኅበራዊ መገናኛቸው ሁሉም ወገኖች በአስቸኳይ ወደ ድርድር እንዲቀርቡ ጠይቀዋል። ዋናው መፍትሔ መንግሥት ሰላምና የዜጎች ደህንነትን ማስጠበቁ ነው ያሉት አስተያየት ሰጪው የአሜሪካ እየተለወጠ ያለ የምሥራቅ አፍሪካ የወዳጅነት አሰላለፍ ኢትዮጵያን ለተጨማሪ ጫና ሊዳርጋት እንደሚችልም ገልፀዋል።
ሰሎሞን ሙጩ
ሸዋዬ ለገሠ
ማንተጋፍቶት ስለሺ