1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሜሪካ ማዕቀብና ግፊት በኢትዮጵያ ላይ

ዓርብ፣ ግንቦት 20 2013

ሴናተር ሮበርት ሜንዴዝ ለሚመሩት ኮሚቴ አባላት እንደነገሩት በኢትዮጵያ ላይ ዓለም አቀፍ የጦር መሳሪያ ማዕቀብ እንዲጣል የባይደን አስተዳደር ዓለም አቀፍ ድጋፍ ማሰባሰብ አለበት።

https://p.dw.com/p/3u7Z6
Demokratischer US-Senator Robert Menendez,
ምስል W. McNamee/Getty Images

 የዩናትድ ስቴትስ መንግሥትና የምክር ቤት እንደራሴዎች በኢትዮጵያና በኤርትራ መንግስታት ላይ የሚያደርጉትን ግፊት እንደቀጠሉ ነዉ።የሐገሪቱ ሕግ መወሰኛ ምክር ቤት (ሴኔት) የዉጪ ግንኙነት ኮሚቴ ሊቀመንበር ትናንት እንዳሉት የኘሬዝደንት ጆ ባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያና ኤርትራ ላይ የጣለዉን ማዕቀብ አጠናክሮ መቀጠል አለበት።ሴናተር ሮበርት ሜንዴዝ ለሚመሩት ኮሚቴ አባላት እንደነገሩት በኢትዮጵያ ላይ ዓለም አቀፍ የጦር መሳሪያ ማዕቀብ እንዲጣል የባይደን አስተዳደር ዓለም አቀፍ ድጋፍ ማሰባሰብ አለበት።የአንትላንታዉ ወኪላችን ታሪኩ ኃይሉ ያነጋገራቸዉ አንድ ኢትዮጵያዊ-አሜሪካዊ የሕግ ባለሙያና የፖለቲካ ተንታኝ ደግሞ የአሜሪካኖችን አቋም ለማስለወጥ የኢትዮጵያ መንግስትም ኢትዮጵያዊያን አሜሪካዉያንም እንዲጥሩ መክረዋል።

ታሪኩ ኃይሉ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ