የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴኃን) የምርጫ ዝግጅት
ሰኞ፣ ጥር 17 2013ማስታወቂያ
ቀጣዩ ብሔራዊ ምርጫ ነፃና ፍትሀዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴኃን)አስታወቀ።ፓርቲው ትናንት ከአባላቱ ጋር በባህርዳር ባካሄደው ውይይት ማንኛውንም የአመፅ እንቅስቃሴ እንደሚቃወም ገልጾ፣ አባላቱና ደጋፊዎቹም ከዚህ እንዲቆጠቡ ግንዛቤ እያስጨበጥኩ ነው ብሏል። ዲሞክራሲ እንዲያሸንፍ እንሰራለን የሚለው ፓርቲው በምርጫ ቢሸነፍ እንኳን በጸጋ ተቀብሎ በቀጣዩ ምርጫ ጠንካራ ተፎካካሪ የሚሆንበትን መንገድ እንደሚፈልግ አስታውቋል።ከሁለት ዓመት በፊት ኢትዮጵያ የገባው የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴኃን) በዘንድሮው ምርጫ ፓርቲው ወክለው የሚወዳደሩ 414 እጩ ተወዳዳሪዎችን አንደሚያቀርብ አስታውቋል። አለምነው መኮንን ከባህርዳር ቀጣዩን ዘገባ አዘጋጅቷል።
አለምነው መኮንን
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ