1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአማራ ክልል ነዋሪዎች ከመጪው መንግሥት ምን ይጠብቃሉ?

ዓርብ፣ ሰኔ 18 2013

ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው የክልሉ ነዋሪዎች በምርጫ አሸንፎ መንግሥት የሚመሠርተው አካል የኅብረተሰቡን ሰላም ፈላጊነት አይቶ ለሰላምና ማሕበራዊ ደህንነት እንዲሠራ ጠይቀዋል። አርሶ አደሮች ለግብርና መዘመን እንዲሰራ፣ የከተማ ነዋሪዎች ደግሞ ለሰላምና ለገበያ መረጋጋት እንዲሠራ፣ ልጆችም በበኩላቸው የስፖርት ማዘውተሪያ ትኩረት እንዲሰጠው ይፈልጋሉ።

https://p.dw.com/p/3vZWP
Äthiopien Bahir Dar | Wahlergebnisse
ምስል Alemnew Mekonnen/DW

ከተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎች የተሰባሰበ አስተያየት

የዘንድሮው ምርጫ በዓይነቱ ሰላማዊ እንደነበር የገለጹ የአማራ ክልል ነዋሪዎች የሚመሠረተው መንግሥት የኅብረተሰቡን መሠረታዊ ፍላጎት እንዲመለከት አሳሰቡ። ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው የክልሉ ነዋሪዎች በምርጫ አሸንፎ መንግሥት የሚመሠርተው አካል የኅብረተሰቡን ሰላም ፈላጊነት አይቶ ለሰላምና ማሕበራዊ ደህንነት መሥራት ይኖርበታልም ብለዋል። አርሶ አደሮች አዲሱ መንግሥት ለግብርና መዘመን እንዲሰራ ሲጠይቁ የከተማ ነዋሪዎች ደግሞ ለሰላምና ለገበያ መረጋጋት እንዲሠራ አሳስበዋል። ልጆች በበኩላቸው የስፖርት ማዘውተሪያ ትኩረት እንዲሰጠው ይፈልጋሉ። ዶይቼ ቬለ በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ከሚሴ ከተማ፣ አዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ቻግኒ ከተማ፣ የባሕር ዳር ከተማና በምዕራብ ጎጃም ዞን ደዋሮ ቀበሌ ገበሬ ማሕበር የነዋሪዎችን አስተያየት ጠይቋል። አስተያየት ሰጪዎቹ በአጠቃላይ ቅድሚያ መሰጠት አለበት ያሉትን ጉዳይ መንግሥት ቅድሚያ እንዲሰጠው ነው ያመለከቱት።

ዓለምነው መኮንን

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ