1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአቶ ተመስገን ጥሩነህ የመልካም ምኞት መግለጫ 

ማክሰኞ፣ ጳጉሜን 5 2011

በ2011 ባወጧቸው መግለጫዎች ስለተካሰሱት ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ(ሕወሓት)ና የአማራ ዴሞክራሲዊ ፓርቲ (አዴፓ)ግንኙነት ተጠይቀው«ችግሮቻችንን በውይይት ለመፍታት ዝግጁ ነን »ብለዋል።በ2012 ትኩረት ከሚሰጣቸው ጉዳዮች መካከል ለወጣቶች የሥራ እድል መፍጠርና ለክልሉ ከፍተኛ የገቢ ምንጭ የሆነውን የቱሪዝም ዘርፍ ማጠናከር መሆኑንም ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/3PLSQ
Temesgen Tiruneh Äthiopien Regionalregierung
ምስል DW/A. Mekonnen

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የመልካም ምኞት መግለጫ 

በ2012 ዓመተ ምህረት የአማራ ክልል ለሰላም ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አስታወቁ፡፡ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስሀን ጥሩነህ አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ዛሬ በሰጡት የመልካም ምኞት መግለጫ  በተገባደደው 2011  የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት የተገደሉበት ዓመት እንደነበር አስታውሰው ህዝቡ ከዚህ ሀዘን ወጥቶ በመጪው ዓመት ሰላም ለማስፈን የድርሻውን እንዲወጣ አሳስበዋል፡፡ በ2011 ባወጧቸው መግለጫዎች ስለተካሰሱት ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) እና የአማራ ዴሞክራሲዊ ፓርቲ (አዴፓ)ግንኙነት ተጠይቀው «ችግሮቻችንን በውይይት ለመፍታት ዝግጁ ነን »ብለዋል።በመጪው ዓመት ትኩረት ከሚሰጣቸው ጉዳዮች መካከል ለወጣቶች የሥራ እድል መፍጠር እና ለክልሉ ከፍተኛ የገቢ ምንጭ የሆነውን የቱሪዝም ዘርፍ ማጠናከር መሆኑንም ተናግረዋል።መግለጫውን የተከታተለው የባህርዳሩ ወኪላችን አለምነው መኮንን ዝርዝሩን አዘጋጅቷል። 
አለምነው መኮንን
ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ