1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአማራ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር መገደላቸው ተረጋገጠ

እሑድ፣ ሰኔ 16 2011

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር አምባቸው መኮንን እና የርዕሰ መስተዳድሩ የአደረጃጀት ዘርፍ አማካሪ አቶ እዘዝ ዋሴ መገደላቸውን የአማራ ክልል ቴሌቪዥን ጣቢያ አረጋገጠ። የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሆነው የተሾሙት አቶ ምግባሩ ከበደ በጥይት ቆስለው ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል።

https://p.dw.com/p/3KvhB
Äthiopien l Dr Ambachew Mekonnen
ምስል DW/A. Mekonnen

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር አምባቸው መኮንን እና የርዕሰ መስተዳድሩ የአደረጃጀት ዘርፍ አማካሪ አቶ እዘዝ ዋሴ መገደላቸውን የአማራ ክልል ቴሌቪዥን ጣቢያ አረጋገጠ።

የክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በሰበር ዜናው ይፋ እንዳደረገው ከወራት በፊት የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሆነው የተሾሙት አቶ ምግባሩ ከበደ በጥይት ቆስለው ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል።

ጣቢያው ከዚህ ውጭ በዝርዝር ያለው ነገር የለም። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ትላንት ከእኩለ ለሊት በኋላ በብሔራዊው ቴሌቪዥን ቀርበው በሰጡት መግለጫ የአማራ ክልል ባለስልጣናት የተገደሉት እና የቆሰሉት በስብሰባ ላይ እያሉ እንደነበር መናገራቸው አይዘነጋም።