1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአማራ ትግራይ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ወቅታዊ ሁኔታ 

ማክሰኞ፣ ኅዳር 1 2013

የፀገዴ ወረዳን የአማራ ክልል ልዩ ኃይሎች ከተቆጣጠሩት በኋላ የአካባቢዉ ነዋሪዎች ወደመደበኛ ኑሯቸው እየተመለሱ መሆኑ ተናገሩ። በአማራ ክልል የጠገዴ ወረዳ መስሪያ ቤቶችም ሥራ እየጀመሩ እንደሆነ ነዋሪዎች ገልፀዋል፡፡ በራያ ቆቦ በኩል ያለው ሁኔታ ዉጥረt ያንዣበበት ከመሆኑ ዉጭ የተለየ ነገር እንደሌለም ነዋሪዎች አመልክተዋል፡፡ 

https://p.dw.com/p/3l6a6
Äthiopien | Zentral Gonde
ምስል Alemnew Mekonnen/DW

ኅብረተሰቡ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ እየተመለሰ ነዉ

የፀገዴ ወረዳን የአማራ ክልል ልዩ ኃይሎች ከተቆጣጠሩት በኋላ የአካባቢዉ ነዋሪዎች ወደመደበኛ ኑሯቸው እየተመለሱ መሆኑ ተናገሩ። በአማራ ክልል የጠገዴ ወረዳ መስሪያ ቤቶችም ሥራ እየጀመሩ እንደሆነ ነዋሪዎች ገልፀዋል፡፡ በራያ ቆቦ በኩል ያለው ሁኔታ ዉጥረt ያንዣበበት ከመሆኑ ዉጭ የተለየ ነገር እንደሌለም ነዋሪዎች አመልክተዋል፡፡ 

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና የትግራይ ልዩ ኃይል ግጭት ከፈጠሩባቸው አካባቢዎች መካከል አንዱ የፀገዴና ጠገዴ አካባቢ ነው፡፡ የፀገዴን ወረዳ የመከላከያ ሰራዊትና የአማራ ክልል ልዩ ኃይሎች ከተቆጣጠሩት በኋላ ህብረተሰቡ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ እየተመለሰ እንደሆነና የከተማዋ ሰላም እንዲጠበቅ ስምሪት መሰጠቱን “ከተማ ንጉስ” ከተባለቸው የወረዳዋ ማዕከል አንድ አስተያየት ሰጪ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። ኅብረተሰቡም ለመከላከያ ሰራዊትና ለአማራ ልዩ ኃይል ድጋፍ እደረገ እንደሆነም አመልክተዋል።  

ዛሬ የገበያ ቀን በመሆኑም ሆቴሎችም ተከፍተው ኅብረተሰቡ በነፃነት ሰላማዊ ኑሮውን መኖር ጀምሯል ብለዋል የአካባቢው ነዋሪዎች። እንደዚሁም በአማራ ክልል በኩል የጠገዴ ወረዳ ማዕከል ቅራቅር ከተማ ያሉ ቢሮዎች በነበረው አለመረጋጋት ምክንያት ሥራ አቁመው የነበሩ ቢሆንም አሁን ስራ መጀመራቸውን የከተማዋ ነዋሪ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። በትግራይ ክልል አላማጣና በአማራ ክልል ቆቦ በኩል ያለው ሁኔታ ከውጥረት በስተቀር የተለየ ነገር እንደሌለ አንድ የከተማው ነዋሪ አመልክተዋል፡፡ ባንኮች ለአገልግሎት ክፍት ባይሆኑም አንዳንድ መስሪያ ቤቶች ክፍት መሆናቸውንም ገልፀዋል። በአማራ ክልል ስር የምትገኘው የቆቦ ከተማና በትግራይ ክልል ስር የምትገኘው አላማጣ ከተማ በቅርብ እርቀት ላይ የሚገኙ ከተሞች ናቸው። 

ዓለምነው መኮንን

አዜብ ታደሰ 

ሸዋዬ ለገሠ