1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ መግለጫ

ረቡዕ፣ ጥቅምት 25 2013

የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ፦ የፌደራል እና የኦሮሚያ ክልል መንግሥታት እንዲሁም ብልፅግና ፓርቲ ዜጎችን ከጥቃት የመከላከል ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ባለመወጣታቸው በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቁ፣ ጥፋተኞች በዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲጠየቁና ተጎጅዎች እንዲካሱ ብሎም መሰል ጥቃት ዳግም እንዳይከሰት ዋስትና እንዲሰጡ  ጠየቀ።

https://p.dw.com/p/3ksTB
Äthiopien | Kraftstoffknappheit  in Bahrdar
ምስል DW/A. Mekonnen

ጥፋተኞች በዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲጠየቁ ብሏል

የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ፦ የፌደራል እና የኦሮሚያ ክልል መንግሥታት እንዲሁም ብልፅግና ፓርቲ ዜጎችን ከጥቃት የመከላከል ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ባለመወጣታቸው በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቁ፣ ጥፋተኞች በዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲጠየቁና ተጎጅዎች እንዲካሱ ብሎም መሰል ጥቃት ዳግም እንዳይከሰት ዋስትና እንዲሰጡ  ጠየቀ። መማክርት ጉባኤው የችግሩ ምንጭ ሕገ መንግሥቱ የፈጠረው አግላይ መንግሥታዊ ስርዓት መሆኑን ጠቅሶ ዘላቂ መፍትሄ እንዲገኝ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሕገ መንግሥቱ እስኪሻሻል ድረስ ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት መከላከል የሚያስችል እና የአናሳ ሕዝብ የፖለቲካ እና የአስተዳደር ውክልና እንዲኖር የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ እንዲያወጣ እና ይህንኑ የሚያስፈጽም ተቋም እንዲቋቋም ጠይቋል። ጥፋተኞች በዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲጠየቁና ተጎጅዎች እንዲካሱ፤ ብሎም መሰል ጥቃት ዳግም እንዳይከሰት ዋስትና እንዲሰጡም ሲል ጉባኤው ትናንት በጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ ማሳሰቡን የአዲስ አበባው ወኪላችን ሰለሞን ሙጬ የላከልን ዘገባ ይጠቁማል።

ሰለሞን ሙጬ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
እዘቴ በቀለ