1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሚልካር ካብላር የጋራ ነፃነት

Merga Yonas Bula
ሐሙስ፣ ሐምሌ 19 2010

አሚልካር ካብላር ጊኒ ቢሳዉ እና ኬፕ ቨርዴን ወደ ነጻነት ለመምራት በጣም ወሳኝ ሰው የነበሩ የ20ኛው ክፍለ ዘመን የአፍሪቃ ፋላስፋ ናቸዉ። ነፃ ለመውጣት ትምህርት በጣም ወሳኝ የመሳሪያ እንደሆነ ቢገነዘብም፤ ካቡራል የፖርቹጋል ቅኝ ገዢዎችን ለመታገል ጠብመንጃን ለማንሳት ወደኋላ አላለም።

https://p.dw.com/p/30Tqe
African Roots Amílcar Cabral
ምስል Comic Republic

እንደ አዉሮጵያዊያን አቆጣጠር በ1959 ዓ/ም ጊኒ ቢሳዉ ውስጥ ተቃዉሞ ባነሱ የመርከብ ሠራተኞች ላይ የፓርቹጋል ባለሥልጣናት ተኩስ ከፍተው 50 ሰዎችን በመግደል በመቶዎች የሚቆጠሩ ሌሎች ሰዎችን አቁስለዋል። የፕድጅጉቲ ጭፍጨፋ በመባል የሚታወሰው ይህ ክስተት ለአሚልካር ካብላር ወሣኝ ወቅት ነበር። ከዚያም እሱ የመሠረተው ፕ ኤ አይ ጅ ስ የተባለዉ ፓርቲ ጠብመንጃ እንዲያነሱ ጥሪ አደረገ።

የጊኒዉ ጋዜጠኛ ቶኒ ቼካ እንደሚለው ከሆነ፤ «አሚልካር ካብላር የሰላም ሰዉ ነበረ። ወደ ጦርነት የገባው ሰላምን ለመጎናፀፍ ነዉ።»

DW Videostill Projekt African Roots | Amílcar Cabral, Guinea Bissau, Kapverden
ምስል Comic Republic

እንደ አዉሮጳ አቆጣጠር በ1924 ጊኒ ቢሳው የተወለደ ካብራል በልጅነቱ ወደ ኬፕ-ቨርዴ በመሄድ ትምህርቱን እዛዉ አጠናቀቀ። ከዚያም ፖርቹጋል ውስጥ የዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን መማር የሚያስችል የነፃ ትምህርት እድል አገኘ። በቆይታውም የአብዮት ንቅናቄዎችን ካመሩ አሜሪካውያን ጋር ጓደኝነትን ፈጠረ። ወደሀገሩ ሲመለስም በፖርቹጋል ቅኝ ገዢ ባለስልጣናት ስር ተቀጥሮ በግብርና ኤኮኖሚ ዘርፍ ሠርቷል።

ይህ አጋጣሚም ስለሕዝቡ የከፋ ድህነት እንዲረዳ ዕድል ስለሰጠው ጊኒ ቢሳዎ እና ኬፕ ቨርዴ ነፃ እንዲወጡ ቅስቀሳ ያደርግ ጀመር። ሁለቱ ሃገራት ነፃ እስኪሆኑ መጠበቁ ለካብሪል ምክንያታዊ ርምጃ ነበር ይላል ጋዜጠኛው ቼካ፤ «የጊኒ-ቢሳው እና የኬፕ-ቨርዴ ኅብረት የመፍጠር ሃሳብ የመጣዉ ካብራል ስለሁለቱም አገሮች ካለዉ እዉቀት የመነጨ ነዉ። ካብራል የኬፕ-ቬርደዎቹን እውቀት ከጊኒ ቢሳዉን ወሳኝነትና የውጊያ እውቀት ጋር ማቀናጀት ፈልጎ ነበር።»

የካብራል ፅሁፎችና ጽንሰ ሐሳቦች በአህጉሪቱ በሙሉ በመስፋፋት ለሌሎች የአፍሪቃ ነጻነት ንቅናቄ የመነሻ ምንጭ መሆኑን የኬፕ-ቨርዴ የዘር-ሐረግ ያላቸዉና የታርክ ተመራማሪዋ ፖርቱጋላዊ  ሶኒያ ቦርጌስ ይናገራሉ። ቦርጌስ፤ «ለአሚራል ካብራል አለማቀፋዊነትና የአለማቀፍ ትብብር ሁሌም በጣም አስፈላጊዎች ነበሩ። በተለይም እሱ የነፃነት ትግልን እንደ ጋራ ሂደት አድርጎ ማሰቡና እያንዳንዱ ትግል የራሱ የተወሰነ ብሔራዊ ባህሪያት የሚለው አስተሳሰቡ፤ በተለያዩ አውዶች ካብራል እንዲጠቀስ አድርጓል።»

DW Videostill Projekt African Roots | Amílcar Cabral, Guinea Bissau, Kapverden
ምስል Comic Republic

በካብራል መሪነት፤ ፕ ኤ አይ ጅ ስ ፓርቲ እንደ አዉሮጵያውያን አቆጣጠር በ1963 በፖርቹጋል ላይ በመሳርያ የታገዘ ትግል ተጀመረ።  ከፍተኛ ድጋፍም ከኩባ፤ ከቻይና እና ከሶቪየት ኅብረት ያገኙ ነበር። ሆኖም ግን  የእነዚህን ሀገሮች ርዕዮተ ዓለምን ለመቀበል ካብራል ፈቃደኛ አልነበረም። እሱ የፈለገዉ በአካባቢው ፍላጎቶች የተቃኘች ነፃ የሆነች ጊኒ ቢሳዉን መገንባት እንጂ የውጭ ሐሳብ መዉሰድ አይደለም። ጋዜጠኛ ቼካ የካብራል አባባሎችን ይጠቅሳል፤ «እርዳታ የምንቀበልበት ብቸኛው ሁኔታ እነሱ እኛን ላይ ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታዎች እንዳይጭኑ ነው።»

ካብራል እንደ አውሮጳውያን አቆጣጠር በ1973 ቢገደልም ለነፃነት የነበረው ትግል ግን ጊኒ ቢሳዉ በ1974 እና ኬፕ-ቨርዴ በ1975 ነጻነታቸዉን እስከሚጎናፀፉ ድረስ ቀጥሎ ነበር።

 

መርጋ ዮናስ

ካርላ ፌርናንዴስ

ሸዋየ ለገሰ 

 ይህ ዘገባ አፍሪካዊ ሥረ-መሠረት በሚል ከጌርዳ ሔንክል ተቋም ጋር በመተባበር የሚቀርብ ልዩ ዝግጅት አንድ አካል ነው።

 This report is part of African Roots, a project realized in cooperation with the Gerda Henkel foundation.