የአሌ ልዩ ወረዳ ምክር ቤት የቀረበለትን አስተዳዳሪ ሹመት ውድቅ አደረገ
ዓርብ፣ ጥቅምት 12 2014ማስታወቂያ
በደቡብ ክልል የአሌ ልዩ ወረዳ ምክር ቤት አስቸኳይ ገባኤ በገዢው ፓርቲ የቀረበለትን የወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ሹመት በአብላጫ ድምፅ ውድቅ አደረገ ።
ምክር ቤቱ የዋና አስተዳዳሪውን ሹመት ሳይቀበለው የቀረው በእጩነት የቀረቡት ግለሰብ የማስፈጸም አቅም የላቸውም በሚል መሆኑን የልዩ ወረዳው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ገኒሶ ገሳቶ ለዶቼ ቬለ (DW) ገልጸዋል። ዶቼ ቬለ (DW) ያነጋገራቸውና ሹመቱ ውድቅ የተደረገባቸው እጩ በበኩላቸው የምክር ቤቱን ውሳኔ የሚቀበሉት ቢሆንም በሂደቱ ግን አሻጥር ተሰርቶብኛል ይለሉ።
ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ
ታምራት ዲንሳ
ነጋሽ መሐመድ