1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኔቶ ጉባዔ፤ ባይደን እና የፑቲን ዉይይት

ረቡዕ፣ ሰኔ 9 2013

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንና ከሩስያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጄኔቫ ስዊትዘርላንድ ውስጥ ዛሬ ጉባዔ አካሄዱ። ሁለቱ መሪዎች ውይይታቸው የሃገራቱን ግንኙነት ወደተሻለ የሚያመራ ይሆናል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል። መሪዎች በተወያዩበት አካባቢ ኢትዮጵያዉያን ሰልፈኞች የአሜሪካንን ጣልቃ ገብነት በመቃወም ሰልፍ ወጥተዋል።

https://p.dw.com/p/3v2t9
Schweiz Gipfeltreffen USA Russland in Genf
ምስል Denis Balibouse/REUTERS

 

የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት «ኔቶ» በድርጅቱ ታሪክ ዉስጥ ወሳኝ ያለዉን  ጉባዔ ከትናንት ወድያ ሰኞ በድርጅቱ ጽ/ቤት ብረስልስ አካሂዶ ዉሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቆአል። ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የተኩዋቸዉ ትራምፕ ፤  የኔቶችን ብቃት እና አስፈጊነት ከጥያቄ ዉስጥ በማስገባት፤ የድርጅቱን ህልዉና ከጥያቄ ዉስጥ አስገብተዉ የነበረ መሆኑ የሚታወስ ነዉ።  የትናንቱ የኔቶ ስብሰባ እና ቀደም ሲል የተጠናቀቀዉ የቡድን ሰባት ጉባዬ  የትራምፕ አስተሳሰብ የተቀለበሰበት እና የትራምፕ ዓለም አአፋዊ ተሳትፎ የተመለሰበት ነዉ ተብሎአል።  የኔቶ ጉባዔ በተሰታፊዎቹም በአጀንዳዎቹም ከአንድ ቀን ቀደም ብሎ ፤ በብሪታንያ የተካሄደዉ የቡድን ሰባት ቀጣይ ስብሰባ ሆኖ ተስተዉሎአል። በሌላ በኩል የዩናትድ ስቴትሱ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን እና የሩስያዉ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዛሬ ስዊዘርላንድ ጄኔቭ ላይ ተገናኝተዉ ተወያይተዋል።

ገበያዉ ንጉሴ  

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ