1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኔቶ ጉባኤና አዲሱ መመሪያው

ረቡዕ፣ ሰኔ 22 2014

ማድሪድ ስፔይን የተሰበሰቡት የቱርክን ጨምሮ 30 የድርጅቱ አባል ሀገራት መሪዎች የስዊድንና የፊንላንድን እጩነትን ተቀብለዋል። ኔቶ በዛሬው ጉባኤው በአዲሱ የጸጥታ መርሁ ከአሁን በኋላ ሩስያን እንደ ቀድሞው ስልታዊ አጋር እንደማያያት አስታውቋል።ዩናይትድ ስቴትስ ከሩስያ የሚሰነዘር ጥቃትን ለመመከት ተጨማሪ ሠራዊት አውሮጳ አሰፍራለሁ ብላለች።

https://p.dw.com/p/4DR0E
NATO Gipfel in Madrid
ምስል Kenny Holston/Pool/AP/picture alliance

የኔቶ ጉባኤና አዲሱ መመሪያው

የሰሜን አትላንቲክ የጋራ መከላከያ ቃል ኪዳን ድርጅት በምህጻሩ ኔቶ የስዊድንና የፊንላንድ የኔቶ አባልነት ሂደት በይፋ መጀመሩን አስታወቀ። ዛሬ ማድሪድ ስፔይን የተሰበሰቡት የቱርክን ጨምሮ 30 የድርጅቱ አባል ሀገራት መሪዎች የሁለቱን ሀገራት እጩነትን ተቀብለዋል። ኔቶ በዛሬው ጉባኤው በአዲሱ የጸጥታ  መርሁ ከአሁን በኋላ ሩስያን እንደ ቀድሞው ስልታዊ አጋር እንደማያያት አስታውቋል።ዩናይትድ ስቴትስ ደግሞ ከሩስያ የሚሰነዘር ጥቃትን ለመመከት ተጨማሪ ሠራዊት አውሮጳ እንደምታሰፍር አስታውቃለች። የድርጅቱ ፈጥኖ ደራሽ ጦርም ከ40 ሺህ ወደ 300 ሺህ ከፍ እንዲል አቅዷል። 

ይልማ ኃይለ ሚካኤል 
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ