1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኤኮኖሚኢትዮጵያ

የኑሮ ውድነት በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 18 2014

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የዋጋ ጭማሪ ነዋሪዎችን እያስመረረ ነው። ከዚህ ቀደም 20 ብር የነበረ አንድ ኪሎ ሽንኩርት 45 ብር በሚሸጥበት ክልል ዘይት እና ስኳር የመሳሰሉ መሠረታዊ ፍጆታዎች ዋጋ ጭማሪ ማሳየቱን ተናግረዋል። በነዳጅ ማደያዎች የሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ሰልፍ ማየት የተለመደ መሆኑን የዶይቼ ቬለው ነጋሳ ደሳለኝ ዘግቧል። 

https://p.dw.com/p/4ASIe
Asosa, West-Äthiopien und Hauptstadt der Region Benishangul-Gumuz
ምስል privat

የኑሮ ውድነት በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል

የፍጆታ ዕቃዎች እና የቁም እንስሳት ዋጋ መጨመሩን የአሶሳ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ ያነጋገርናቸው ነዋረዎች በሰጡን አስተያየት በሽንኩርት፣ስኳርና  የተለያዩ ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ ተደርጓል፡፡ በኪሎ 25 ብር የነበረ የሽንኩርት ዋጋ እስከ 45 ብር፣55 ብር የነበረው የስኳር ዋጋ 65 ብር መድረሱን የተናገሩት ነዋሪዎቹ የቤንዚን እና ናፍጣ ዋጋም መጨመሩን ወይም በተለምዶ ጥቁር ገበያ በሚባለው በድብቅ አንድ ሊትር እስከ 100 ብር እየተሸጠ እንደሚገኝ አክለዋል፡፡ በአሶሳ ከተማ የቁም እንስሳት ዋጋም ዘንድሮ  በከፍተኛ  ሁኔታ መጨመሩን ሸማቾችና አቅርቢዎች ተናግረዋል፡፡ የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት እየሰራ እንደሚገኝና ምርት በሚደብቁ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ የክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሰሞኑን በሰጠን ማብራሪያ አመልክተዋል፡፡

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ የክልሉ ወረዳዎች የፍጆታ ምርቶች፣የግባንታ ዕቃዎች እና የቁም እንስሳት ዋጋ ወትሮ ከነበረው የአንድ አንዱ ዋጋ በእጥፍ መጨመሩን ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ በአሶሳ ከተማ ከዚህ ቀደም በ20 ብር ሲሸጥ የነበረው የአንድ ኪሎ ሽንኩርት ዋጋ 45 ብር እየተሸጠ መሆኑን የነገሩን ነዋሪዎቹ የዘይት፣ስኳርና ሌሎችም ምርቶች ዋጋ ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየታቸውን አብራርተዋል፡፡ በሸማቶች ማህበር ይቀርቡ የነበሩ በተለይም እንደ ስኳርና ዘይት ያሉ ምርቶች በአሁኑ ጊዜ አቅርቦት በተወሰኑ ስፍራዎች መቋረጡን ይገልጸዋሉ፡፡
ከፍጆታ ዕቃዎቸ በተጨማሪም ከዚህ ቀደም 20ሺ ብር የነበረው የአንድ መለስተኛ በሬ ዋጋ 40ሺ መድረሱንና  በአሶሳ ከተማ እስከ 78ሺ ብር አንድ በሬ በበዓል ወቅት ተሽጧል፡፡ የዋጋ ጭማሪውን አንድ አንዶች ከአቅርቦት እጥረት ጋር ተያይዞ እንደሆነ ሲገልጹ ሌሎች ደግሞ ከእንስሳት መኖ ዋጋ መጨመርና የዜጎች ወደ ፈለጉበት አካባቢ በነጻነት መዘዋወር አለመቻልና ከጸጥታ ችግር የመነጨ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
የቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ የዋጋ ንረቱን ለማጋጋጋት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ የቢሮው ኃላፊ አቶ ለሜሳ ዋቅወያ ባለፈው ሐሙስ በዚሁ ጉዳይ ላይ በሰጡን ማብራሪያ በአንድ አንድ ስፍራዎች የተስተዋሉት የፍጆታ ምርቶች እጥረት ምርቱን ለማፋፈል ኃላፊነት ያላቸው ዩኒየኖች(ማህበራት) በወቅቱ  ባለማከፋፈላቸው የተፈጠረ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
በክልሉ በተለይም በአሶሳ ከተማ ከፍጆታ ምርቶች በተጨማሪ የቤንዚንና ናፍጣ እጥረት ባለፉት ወራት ዋጋቸው በእጥፍ መጨመሩንና አንድ ሊትር በ100 ብር  እየተሸ እንደሚገኝ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ በከተማው ለነዳጅ ፍለጋ የተሰለፉ ረጃጅም የተሽከርካሪ ስልፎች በተለይም ባለሶስት እግር ተሽከርካሪ ባጃጆችን ሰልፍ ማየት የተለመደ እየሆነ ነው፡፡ ይህንን ችግር ለመፍታት ከነዳጅ አቅራቢ ድርጅቶች ጋር እየተነጋገረ እንደሚገኝ የክል ንግድ ቢሮ ለዲዳቢሊው ገልጸዋል፡
ነጋሳ ደሳለኝ
እሸቴ በቀለ
አዜብ ታደሰ