1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኑሮ ዉድነት፤ ሰዉን በቁሙ የማቃጣል ጭካኔ፤ የሩስያ ዩክሬይን ጦርነት

ዓርብ፣ መጋቢት 9 2014

ኢትዮጵያ ዉስጥ የኑሮ ውድነቱ ማህበራዊና ፖለቲካዊ መፍትሄ ያስፈልገዋል። ባለፈዉ ሰሞን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ይፋ ባደረገዉ መግለጫ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሰዎች አስከሬን እና አንድ ሰው በህይወት እያለ በቁሙ በእሳት መቃጠሉ፤ እንዲሁም የሩስያ ዩክሬይን ጦርነት፤ አስተያየት ያሰባሰብንባቸዉ ርሶች ናቸዉ።

https://p.dw.com/p/48hU0
Social Media Apps | WhatsApp Facebook Twitter Instagram
ምስል Nasir Kachroo/ZUMA Press/imago images

የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት

ኢትዮጵያ ዉስጥ የኑሮ ውድነቱ ማህበራዊና ፖለቲካዊ መፍትሄ ያስፈልገዋል፤ በሃገሪቱ ዉስጥ የሸቀጦች ዋጋ መጨመር፣ የኑሮ ውድነት እንዲባባስ ምክንያት እየሆነ ይገኛል፤ ሲሉ ዜጎች ያማርራሉ። የዋጋ ጭማሪው በተለይ አብዛኛው የማህበረሰብ ክፍል ሸማች በሆነባቸው የከተሞች አካባቢ የዜጎች እለታዊ ኑሮ እንዲከብድ አድርጎታል ነው የሚባለው።

አንድ ስማቸዉን በቻይንኛ በመሰለ ፅሁፍ መለያ ያደረጉ የዶቼ ቬለ የፊስቡክ ተከታታይ የኑሮ ዉድነቱ ሆን ተብሎ የሚደረግ አሻጥር ነው፡ ሲሉ ይጀምራሉ አስተያየታቸዉን። የኑሮ ዉድነቱ ሆን ተብሎ የሚደረግ አሻጥር ነው።  አንዳንድ ስግብግብ የሆነ ነጋዴዎችም ያለ በቂ ምክንያት እና የምርት እጥረት የዋጋ ጭማሪ ሌሎች ስላደረጉት ያደርጋሉ። የተቃዋሚ የፓለቲካ ኃይሎች ፡ በተለይም ሸኔ ፡ ህዋህት የመሳሰሉት ድርጅቶች በሕዝብ ላይ አመፅ እንዲፈጠር እና የኑሮ ዉድነቱ እንዲጋጋል እንደሚያሴሩ አያጠራጥርም ። ይኸም መንግሥት ሆን ብሎ ጉዳዩን መርምሮ፡ መፍትሄ መስጠት ይኖርበታል። ዋጋ በሸቀጦች ላይ በየዕለቱ እየጨመረ የሚሄድ ነገር ሆኗል። መንግሥት የተረጋጋ ሀገር ለመፍጠር የተረጋጋ ሀገራዊ ኢኮኖሚ መፍጠር ይኖርበታል፡ ይኸም መሰረታዊ ፍላጎቶች ላይ ፡ ምግብ ፡ መጠጥ፡ ልብስ የመሳሰሉት ላይ የመንግስት ተቋም ተመስርቶ መንግሥታዊ አገልግሎት ሊሰጥ ይገባል። ዳቦ ቅንጦት የሆነበት ሀገር ዉስጥ ነው ያለነው፤ ሲሉ አስተያተቸዉን ይደመድማሉ።

መማር ከንቱ ያሉት ሶል ናን ጊጊ የተባሉ የፊስቡክ ተጠቃሚ  «አዲስ አበባ ውስጥ የመንግስት ሰራተኛ በኑሮ ውድነት ማበዱ ነው፤ መማር ከንቱ ያስብላል ትግስታችን እያለቀ ነው፤ ብለዋል። ገዳሙ ኩራባቸዉ በበኩላቸዉ፤ፓርቲና ባለስልጣን ንግድ የጀመሩ ቀን እኮ ነው ነገር የተበላሸው፤ሲሉ አስተያየት ፅፈዋል።

Uganda | Smartphone Nutzerin in Kampala
ምስል ISAAC KASAMANI/AFP/Getty Images

ብሩህ ደረስ የተባሉ የፌስ ቡክ ተጠቃሚ ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ወዶ ውሽታሙ እና ገዳዩን ብልፅግናን ተቀብለን የኑሮ ውድነቱ ብቻ ሳይሆን ሞቱንም ተቀብለን እየኖርን ነው። ሌባውም መንግስት ገዳይ አስገዳዩም አፈናቃዩም ብልፅግና ብቻ ነዉ።  ፈጣሪ ያውቃል ስጦናል መቻል ነው፤ ሲሉ  አስተያየታቸዉን ይደመድማሉ።

ከቡልጋርያ ማዞትያ ነኝ ያሉ ወርቅነህ ጌትዬ የተባሉ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ተጠቃሚ፤ የዓለም ዉስጥ ስህተት ሊኖር ይችላል። እውነታው እኛ ጋር ግን ህዝብ ከመቸገሩም በላይ የእለት ጉርሱን አጥቷል። ለመቸገሩ ማስረጃው አደባባይ መውጣት ከሆነ ትንሽ ጠብቁን፤ ሲሉ ነዉ አስተያየታቸዉን የደመደሙት።  

ጉዲሳ አምቦ የኑሮ ዉድነት ትንሽ ቀናት ይሰጣል ሲሉ አስተያየታቸዉን ይጀምራሉ። የኑሮ ዉድነት ትንሽ ቀናት ይሰጣል። በጠራራ ፀሃይ የሰው ልጅ አካልን በእሳት የመጥበስ ነገር ምን ትላላችሁ? እዚህ ላይ የአኖሌ እና የጨለንቆ ፍጅትን የሚያስደንቅ ወንጀል አይደለም ትላላችሁ? በጥያቄ አስተያየታቸዉን ይዘጋሉ።

ፋሲል አምሳሉ የተባሉ የፌስቡክ ተጠቃሚ ደግሞ፤ ሰዉ ከነነፍሱ በእሳት ከሚቃጠልበት ሀገር ላይ ዘይት 1000 ብር ገባ ብሎ መጠየቅ፤ ሲያንሰን ነዉ ገና አንድ 10,000 ብር ይገባል።  በግፍ እየኖርን ደልቶን ልንኖር ያምርሀል?  አትስበዉ እንኳን ጠግበን ተርበንም አልተቻልን ብለዋል።

USA Trumps neue Social Media Plattform "Truth social"
ምስል Muhammad Ata/ZUMAPRESS.com/picture alliance

ሃጎስ ጥዑም የተባሉ የፌስቡክ ተጠቃሚ እብድ ቤቱዋን ሲታቃጥል የበራላት ይመስላታል ተባለ እኮ።   በ27 ዓመት የታየዉ የልማት የኢኮኖሚ ከፍታ በሦስት ዓመት ወደ ቁልቁለት ወደ ጭቃ ወደ ዘሮ ወረደ። እናም አንጨብጭቡ ጥሩ መሪ ጥሩ እድገት ነው።  ከከፍታ ወደ ቁልቁለት ግቡ ሲሉ አስተያየታቸዉን ደምድመዋል። አለሙ አሌክስ የተባሉ የፌስ ቡክ ተጠቃሚ ፤ የኑሮ ዉድነትን ብልፅግና ፈተና አድርጎ አልወሰደዉም። ትናትና ፈተናዎችን በድል ተወጠን ልዕልና ተቀዳጅተናል ብሏል። ስለዚህ ነገሩ ይህ የምስኪኑ ህዝብ ፈተና ብቻ ነዉ ብለዋል።

ባለፈዉ ሰሞን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ይፋ ባደረገዉ መግለጫ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሰዎች አስከሬን እና አንድ ሰው በህይወት እያለ በቁሙ በእሳት መቃጠሉን ዘግናኝ እና አረመኒያዊ ሲል ድርጊቱን ባወገዘበት ዘገባ ስር ከተሰጡ አስተያየቶች መካከል፤ ጌታቸዉ ፍፁም የተባሉ የፌስቡክ ተከታታይ ፤ የስርአቱ ዳኛ ካልተጠየቀ ማን ሊጠየቅ ነው? ይህን ድርጊት የፈጸሙት ላይ እርምጃ እንወስዳለን፤ ብሎ እንዲያላግጥ ሳይሆን ከድርጊቱ በፊት ቀድሞ ደርሶ የእዚህን አይነት ጭራቆች ድርጊት ካላከሸፈ ምኑን መንግስት ሆነው፤ ሲሉ አስተያየታቸዉን ይደመድማሉ።

ሀገረ ኢትዮጵያ አሁን አሁን ለዜጎቿ ስዖል እየሆነች ነዉ ሲሉ አስተያየታቸዉን እያሱ ሻንቆ ጫሚሳ በመቀጠል፤  ህግና መንግሥት ባለበት አገር ፈፅሞ መደረግ የሌለበት ተግባር ተፈፅሟል። ለቀጣይ የሃገሪትዋ ዜጎች የመኖር ዋስትና ጥያቄ ውስጥ ገብቷል፤ ይላሉ።  

ይህን ድርጊት የፈፀሙት የመንግስ ፀጥታ ኃይሎች ከሆኑ፤ ለራሳቸው መክሰሱ ምን ትርጉም አለው። ፈጣሪ ፍርድ ይስጥን ሲሉ አስተያየታቸዉን የፃፉት ሰለሞን ገብሪ አባተ ናቸዉ። ሰለሞን ጌታቸዉ በበኩላቸዉ ይጠይቃሉ፤ ሀገርንና ህዝብን ሊጠብቅ ቃል የገባው የፀጥታ ኃይል ለምን በዚህ መልኩ የሰው ልጅ ላይ ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት ያደርጋል፤ እጅግ ያሳዝናል፤ ሲሉ አስተያየታቸዉን ይደመድማሉ።  

ሴናበል ኢትዮጵ የተባሉ የፊስቡክ ተጠቃሚ ፤ ሻሸመኔ ላይ በአደባባይ የተገደለው ወጣትስ፣ ሆዷ ተተርትሮ ህፃኗ ወድቆ የቀረው እናትስ? ፍትህ የሚያገኙት መቼ ነው? ይላሉ። ዮሴፍ አርጋዉ በበኩላቸዉ በአማራክልል በአንድ ቀን ተጨፍጭፈዉ የተገደሉት 168 ሰዎች ጉዳይስ ፤ ስለነዚህ ሰዎች ማን ያስብ? ሲሉ ፅፈዋል።

ወልዱ ሁሉቃ የተባሉ የፌስቡክ ተከታታይ በበኩላቸዉ፤  አኔ ሰዉ በእሳት ተቃጥሎ ይሙት የሚል አይደለሁም። ግን ሰዉ በድሮን (በጦር መሳሪያ) ተቃጥሎ መሞትስ አለበት ወይ?አንዱ አገዳደል ህጋዊ ሌላው ኢህጋዊ። እናስተዉል። ይህ መሣሪያ አምራቾች ያወጡልን ህግ ነዉ። ሲቀጥል እዉነት የፀጥታ አካላት እየተቀረጹ እንደዚህ ያደርጋሉ ወይ? ይህ ነገር ሆን ተብሎ የብሄር ግጭት ለማባባስ የተጠቀሙት ይመስለኛል ለሁሉም ፈጣሪ ቁጣዉን ያብርደዉ ብለዋል።

ሞኪ ሞላ የተባሉ የፌስቡክ ተከታታይ፤ የመንግስት ሚድያ ይህን ዘግናኝ ድርጊት አልገለፁም ለምንድነው ? የተደረገውን እውነታውን ለህዝብ ጆሮ ማድረስ የሚዲያ ሚና ነው።

Russland | Social Media
ምስል Sefa Karacan/AA/picture alliance

ዛሬ 25ኛ ቀኑን በያዘዉ የሩስያ በዩክሬን ላይ የምትፈፅመዉ ወረራና በሮኬት ድብደባ በሽዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል። ከሦስት ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ሃገሪቱን ለቆ ተሰዶአል።  በሩስያ መዲና ሞስኮ እና በሁለተኛዉ ትልቅ ከተማ በሆነችዉ ሳንት ፒተርስበርግ ከተማ ፑቲን የጀመሩትን ጦርነት በመቃወም ዜጎች ለተቃዉሞ ይወጣሉ ይታሰራሉም። በሳምንቱ መጀመርያ ላይ አንዲት ጋዜጠኛ በቴሌቭዥን ቀጥታ ስርጭት የሩስያ በዩክሬን ላይ የጀመችዉን ጦርነት ተቃዉማለች።

ብዙነህ ኦክ ጉዲና የተባሉ የፌስቡክ ተጠቃሚ፤ ጋዜጠኝነት ከባድ ስራ ነው።እውነተኛ ስሜቷን መቆጣጠር አቅቷት ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ ይህች ጀግኒት ሽልማት ይገባታል ሲሉ አስተያየታቸዉን አስቀምጠዋል።  ኤፍሬም ፋራታ የተባሉ አስተያየት ሰጭ በበኩላቸዉ፤ ጀግና ብለናታል። በመንግስትም ሆነ በግል ሚዲያዎች የተሰማራችሁ  ሁሉ ሆ*ም ጋዜጠኞች ከዚህች ልጅ ተማሩ። አስመሳይ አይደለችም ጀግና ለእዉነት የቆመች ጋዜጠኛ ናት፤ ብለዋል።

 

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ