1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ በኢትዮጵያ

ሰኞ፣ ግንቦት 1 2014

የኢትዮጵያ መንግሥት ከትናንት ሚያዚያ 30 ቀን 2014 ዓ.ም አንስቶ የነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ አድርጓል። ለዋጋ ማስተካከያው ምክንያት የሆነው የዓለም አቀፍ የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር እንደሆነ መንግሥት አስታውቋል።

https://p.dw.com/p/4B1ov
Äthiopien | Tanken | Addis Abeba
ምስል S. Muchie/DW

ይህንን የዋጋ ማሻሻያ ተከትሎ በኪሎ ሜትር ርቀት የሚያስከፍሉ እና  የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች የዋጋ ጭማሪ አድርገው ተስተውለዋል። ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው አንድ የፋይናንስ ባለሙያ የነዳጅ ዋጋ መጨመር በኢኮኖሚ ውስጥ በሁሉም ግብአቶችና ምርቶች እንዲሁም አገልግሎቶች ላይ የዋጋ ንረት ከማስከተሉ ባለፈ ቋሚ ገቢ ያላቸውን ዜጎች ኑሮ በእጅጉ ያስወድዳል።
መንግሥት እየደጎመ ከውጭ የሚያስገባውን ነዳጅ በአግባቡ ተቆጣጥሮ ማሰራጨት ቢችል ለዚሁ ሲባል የሚያወጣው ወጪ ብዙ የሚጎዳው አለምሆኑንም ባለሙያው ተናግረዋል። ከትናንት ጀምሮ በተደረገው የነዳጅ የመሸጫ ዋጋ ማስተካከያ በቤንዚን ላይ በሊትር የ 5 ብር ከ13 ሳንቲም እንዲሁም በናፍጣ ላይ በሊትር የ 6 ብር ከ 45 ሳንቲም ጭማሪ ተደርጓል።

ሰለሞን ሙጬ

ልደት አበበ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ