1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት

ዓርብ፣ ነሐሴ 6 2014

«ጉራጌ ሲሰራ ነው የሚያምርበት ለምትሉን፤ ጉራጌ እራሱን በራሱ የማስተዳደር ህገ-መንግስታዊ መብቱን መጠቀም አያምርበትም? ጉራጌ አካባቢውን ማልማት፣ ባህሉን እና ቋንቋውን ማሳደግ አያምርበትም?»

https://p.dw.com/p/4FSut
Symbolbild Facebook & Meta | Pfeil nach unten
ምስል Jakub Porzycki/NurPhoto/picture alliance

የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት

የህዳሴ ግድብ 3ኛ ዙር ውሃ ሙሌት እና ተጨማሪ ተርባይን ስራ መጀመር፣ የጉራጌ ዞን እና ክልል ለማቀር የተጀመረው ሂደት ያስነሳው ውዝግብ እንዲሁም የፌደራል መንግስትና የትግራይ ክልል ድርድር የሚሉት የዛሬው የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የሚያተኩርባቸው ናቸው። የታላቁ የኅዳሴ ግድብ "ዩኒት 9" የተባለ ተርባይን የተሳካ ፍተሻ እና ሙከራ ተጠናቆ  ኃይል ማመንጨት ጀምሯል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ "የታችኛው ተፋሰስ አገራት በድርድር እና በስምምነት ውጤት ማምጣት እንደሚቻል ከልብ አምነው ለዚያ እንዲተጉ" ጥሪ አስተላልፈዋል። ግድቡ የሚያመነጨው ኃይል 750 ሜጋ ዋት ደርሷል። ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ ግብጽ እና ሱዳን በታላቁ ኅዳሴ ግድብ ረገድ "በስምምነት ውጤት" ለሚያመጣ ድርድር እንዲዘጋጁ ጥሪ አስተላልፈዋል። "በታሪክ ውስጥ ማለፍና ታሪክ ሠርቶ ማለፍ የሚባሉ ሁለት ነገሮች አሉ፡፡ በታሪክ ውስጥ ማለፍ ዕድል፣ ታሪክ ሠርቶ ማለፍ ግን ዕድልም ድልም ነው፡፡ ይሄ ትውልድ በዓባይ ግድብ ጉዳይ ባለ ዕድልም ባለ ድልም ነው፡፡ የሺ ትውልድ ጥያቄ በሚመለስበት ዘመን ተገኝቶ ግድቡ ሲገደብ በዓይን ማየት፣ በእጅ መዳሰስ፣ በእግር መርገጥ ባለ ዕድል ሲያደርግ፤ ለግንባታው ገንዘባቸውን፣ ዕውቀታቸውንና ጉልበታቸውን ከለገሡት፣ በዲፕሎማሲና በሚዲያ ለዓባይ ከሚከራከሩት፣ ታሪክ ሠሪ ጀግኖች ወገን መሆን ደግሞ ባለ ድል ያድርጋል፡፡ እነሆ አሁን የሕዳሴ ግድብ ከንድፍ አልፎ፣ ግንባታው ተገባድዶ፣ ግዙፍ ውኃ በጉያው ይዞ ኃይል ማመንጨት ጀምሯል። ዛሬ ዓባይ ተረት ሳይሆን የሚጨበጥ እውነት ነው፤ ከዘፈን-እንጉርጉሮ ወጥቶ ኢትዮጵያን በብርሃኑ ሊያደምቃት፣ ኃይል ሆኖ ሊያበረታት ከጫፍ ደርሷል።

በፈጣሪ ርዳታና በኢትዮጵያዊ ወኔ ሙሉ በሙሉ ግንባታውን አጠናቅቀን የልባችን እንደሚሞላ አልጠራጠርም። እንኳን ደስ ያለን" በማለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። ይህን ተከትሎ በርካታ የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ተጠቃሚዎች እንኳን ደስ ያለን የሚል መልእክት በስፋት እየተንሸራሸረ ነው።
የተወሰኑትን መርጠናል።ሽታ ጽጌ "እንኳን ደስ ያለሽ እምዬ ሀገሬ ሁሌም ከፍ በይልኝ።" ሲሉ ጌታሁን አስፋው ደግሞ "ሀገሬ ኢትዮጵያ የጨለማ ዘመንሽ እያበቃ የብርሃንና የትንሣኤ ዘመንሽ እየመጣ ስለሆነ ደስ ይበልሽ" ሲሉ ጽፏል። ኤልያስ የተባሉ አስተያየት ሰጪ በፌስቡክ "ደ/ር አብይ እንኳን ደሰ አሎት። መላው ኢትዮጲያውያን እንኳን ደሰ አላችሁ። ሀገሬ እምዬ ኢትየጲያ ሰላምሸ ይብዛ። ጠላቶችሸ አንገታቸውን ይድፉ። ቀና በይ ሀገሬ ይህ ጊዜ ያንቺ ነው" ሲሉ በእውቀቱ በላቸውም ተከታዩን ሐሳብ አስፍሯል። "ክብር ለእግዚአብሔር ብቻ ይሁን ደስ ብሎኛል ኢትዮጵያዊ በማሆኔ ብቻ እኮራለሁ ኢትዮጵያ ተስፋ አለት።""እልል በይ ሃገሬ! እኛም የአባቶቻችን ልጆች ስለሆንን ከእድገትና ብልፅግና ጉዟችን የሚገታን ምድራዊ ሃይል የለም። አባይ ከግድብነቱ በላይ አንድነት የማሸነፊያ ሚስጥር መሆኑንና አንድነታችን የበረታ ክንዳችን መሆኑን የሚያሳይ ነው።በተለይ ጠላቶቻችን እና እድገታችንን የማይፈልጉ ሃይሎችን ያሸነፍንበት ነው።" DH የተባሉ በፌስቡክ

"ዓባይ አሁን ምኞት ብቻ አይደለም... ውበትም፣ ኩራትም፣ ጉልበትም፣ ደርማሳዊነትም ነው። ከውበቱ ጭስ አልባ ቱሩፋትነትን፣ ከኩራት መፅናትን፣ ከጉልበቱ አይበገሬነትን እና መልማትን፣ ከደርማሳዊነት አይቀለበሴነት በኮምፓወድ ዳይናሚዝምነት ፈጥረን ወደ ከፍታው እንጓዛለን። እንኳንም ደስ አለን። ሙደ ነጋ የተባሉ ደግሞ "ያቃተን አብሮ መስራት እንጂ አብረን ስንሆን ታሪክ መስራት እንደምንችል ያሳያል!! እንኳን ደስ አለን" የሚል አስተያየት ጽፏል። ኤማ የአቡኪ  "እንኳን ደስ አለን ። የኢትዮጵያ ህዝብ በሀገርም ከባህር ማዶም ያላችሁ በድጋሚ እንኳን ደስ አለን። ከፍተኛ መስዋዕትነት ለከፈላችሁ እየከፈላችሁ ላላችሁ በግድቡ ሥራ ላይ ላላችሁ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ።"ዘነቡ ነጋ ያሰፈሩት አጭር አስተያየት ደግሞ "የኢትዮጵያ ከፍታ ማየት እንዴት ያስደስታል ኢትዮጵያየ እንኳን ደስ አለሽ ትፈርሳለች ተብለሽ ተገንብትሽ አየንሽ ጠላቶችሽን አንገት አስደፍተሽ አየንሽ" ይላል።"ዛሬን በትላንት ውስጥ እያየን ይህ ሁሉ እሙን እንደሚሆን የተመኘነውም፣ ግንባታው ሣይዘገይብን በፍጥነት እንዲጠናቀቅ የጓጓንለትም፣ ካለን ውስን አቅም ቆርሰን በስጦታ መልክ ያበረከትነውም፣ ባለን ጉልበት፣ ሙያና ዕውቀት ግንባታው ከግብ እንዲደርስ የተረባረብነውም ይህንን የድል ቀን ለማየት ነው፡፡እንኳንም ደስ አለን!! ግዛቸው አባተ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች በሙሉ እንኳን ደስ አለን!፤ገዢው ፓርቲ አገራችንን ሪፎርም አድርጎ መምራት ከጀመረ በኋላ የነበሩ ፕሮጀክቶችን ማስቀጠል ብቻ ሳይሆን አዳዲሶችን ጀምሮ የጨረሰ ለውጤት ያበቃ መሆኑን የዛሬው የህዳሴ ግድባችን ሀይል ማመንጨት ዋነኛ ማሳያ ነው።ፕሮጀክቶች የፖለቲካ ማስፈፀሚያነታቸው በማስጀመር ብቻ ሳይሆን ተጨርሰውም አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ "ጀምሮ የመጨረስ፤የተጀመሩትን መጨረስ" ዋነኛ መርህ አድርጎ እየሰራ ይገኛል።ስለሆነም ተጀምረው እንዲያልቁ አገልግሎት እንዲሰጡ ከተደረጉ ሜጋ ፕሮጀክቶች መካከል ህዳሴው አንዱና ዋነኛው ነው።እነሆ ጀመረ!!! እንኳን ደስ አለን! እንደጀመርነው እንጨርሰዋለን!! ህዳሴያችን የኢትዮጵያ ብልፅግና ፈር ቀዳጅ! የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ትላንት  ባካሄደው 4ተኛ ዙር 8ኛ አመት 9ኛ አስቸኳይ ጉባኤ በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ የቀረበውን  ከአጎራባች የዞን መስተዳድሮች ጋር በአንድ የጋራ ክልል ለመደራጀት የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ሳይቀበለው ቀረ ፡፡ ምክረ ሀሳብ በምክር ቤቱ አባላት ሰፊ ውይይት ከተደረገ በኃላ በ40 ድጋፍ በ52 ተቃውሞ የውሳኔ ሀሳቡ ውድቅ አድርጓል። 
በምክር ቤቱ ውድቅ የተደረገው የውሳኔ ሃሳብ የጉራጌ ዞንን ከሃድያ ፣ ከሥልጤ ፣ ከሃላባ ፣ ከከንባታ ጠንባሮ ዞኖችና ከየም ልዩ ወረዳ ጋር በአንድ ክልል ለማደራጀት የሚጠይቅ እንደነበረ ታውቋል ፡፡
ቀደም ሲል ከጉራጌ ዞን በስተቀር በደቡብ ክልል የሚገኙ 10 ዞኖችና 6 ልዩ ወረዳዎች በሁለት ተከፍለው ለመደራጀት የሚስችላቸውን ጥያቄ ለአገሪቱ የፌደሬሽን ምክር ቤት  ማቅረባቸውን ይታወሳል፡፡ ምክረሐሳቡ በጉራጌ ዞን ምክርቤት እንዲጸድቅ በገዢው ፓርቲና መንግስት ጫና እየተደረገብን ነው ያሉ የዞኑ ነዋሪዎች ለሁለት ቀናት  ምንም አይነት የንግድ እንቅስቃሴም ሆነ የትራንስፖርት አገልግሎት ባለማካሄድ ሰላማዊ ተቃውሞ ማድረጋቸውንና የታሰሩ ሰዎች እንዳሉም ታውቋል ። በዚህ ጉዳይ ላይ በተለያዩ የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ከተሰነዘሩ በርካታ አስተያየቶች የተወሰኑትን እናቀርባለን። ያቆብ ኤስ አህመድ የተባሉ በፌስቡክ ጉራጌ ሁሉ ሃገሩ ሁሉ ወንድሙ የሆነ ሕዝብ ነው:: ድህነትን በስልጣን ሳይሆን በሥራ ብቻ ማስወገድ እንደሚቻል የሚያምን ለፍቶ አዳሪ ሕዝብ ነው:: የክልል ጥያቄውም መሰረቱ እንዴት አብሮ ማደግ እና እንዴት በፍቅር አብሮ መኖር እንደሚቻል ማሳያ ሜዳ ፍለጋ ብቻ ነው:: ሁሌም ፈገግ በል የተባሉ ሌላ የፌስቡክ ተጠቃሚ

Whatsapp  Logo
ምስል Illia Uriadnikov/PantherMedia

ፖለቲከኞች ለራሳቸው መቀመጫ ሲያመቻቹ ሰርቶ ማደግና መለወጥን አላማው ያደረገውን ህዝብ የማይጠቅመውና ወደ ክስረት የሚመራው ፖለቲካ ውስጥ ከተውት ትለልቅ ችግር  ውስጥ ሊከቱት ይሞክራሉ። እርግጠኛ ሆኜ ምነግራቹ በዚ ሰአት መቼም ብቻውን ክልል መሆን አይችልም። አቡ  በሚል ስም የሚታዎቁት ደግሞ መልዕክት ለመንግስት በማለት ይጀምራሉ። ቀጠሉ የጉራጌ ዞን ፀጥታው ዘርፍ ክልልነት የሚደግፉትን ከለላ እንደሚሰጠው ሁሉ ክላስተር ደግፈው ከመንግስት ጎን ለቆሙት መንግስት ከለላ ሊሰጥ ይገባል። የዞኑ ፀጥታ ሀይልና ከተማ አስተዳደሩ አብራችሁ ሱቅ ዝጉ፣ ትራንስፖርት አቁሙ፣ ስራ አትግቡ፣ ሆቴል አትክፈቱ ብሎ እያስገደደ ነበር። ክለስተር መደገፍ መብት ነው፣ መሀል ከተማ ያላችሁና አብሮነትን ምርጫችሁ ያደረጋችሁ በመብት ጉዳይ ወደ ኋላ የለም፣ ለሰከንድም ቢሆን።መንግስት ክለስተረን አማራጭ ባደረጉት ላይ በዞኑ ፀጥታ ሀይል የሚደረግባቸውን ጫና መከላከል ካልቻለና ህዝቡ መብቴን እራሴ ላስከብር ካለ ጥሩ አይሆንም። የራስህን መብት ስትጠይቅ የሌላውንም ማክበር ግዴታ ነው። ብለዋል። ጁቬ ኤፍሲ ደግሞ ጥያቄ በጥያቄ ላይ ያነባበረ መልእክታቸውን እንደሚከተለው ይቀርባል።

 ጉራጌ ሲሰራ ነው የሚያምርበት ለምትሉን።  ጉራጌ እራሱን በራሱ የማስተዳደር ህገ-መንግስታዊ መብቱን መጠቀም አያምርበትም? ጉራጌ አካባቢውን ማልማት፣ ባህሉን እና ቋንቋውን ማሳደግ አያምርበትም? ጉራጌ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን ለማስጨረስ ወደ ሌሎች አጎራባች ክልሎች እየተመላለሰ ሳይንገላታ "ክላስተር በሚባል" ባልተስማማበት ነገር ሳይታጨቅና ሳይጉላላ እዛው ጉራጌ ክልል ውስጥ በመጨረስ ጊዜውን፣ ጉልበቱን፣ ገንዘቡን.....ሳያባክን በአካባቢው ማስፈፀም አያምርበትም? መብቱን በሚጠይቅ ህዝብ ላይ እንዲህ ብሎ መሳለቅ ልክ ነው?
 መቼነው ከጭፍን ድጋፍና ነቀፌታ፣ ከመጠላላት፣ ከአጉል ፍረጃ ወጥተን እንደሰው ከእውነት እና ከፍትህ ጎን የምንቆመው?  የጉራጌን ህዝብ እራስን በራስ የማስተዳደር ህገ- መንግስታዊ መብት በመደገፍ ከጎናችን ለቆማችሁ ውድ የኢትዮዽያ ልጆች ለእናንተ ያለኝን አክብሮት በራሴና በጉራጌ ህዝብ ስም ከልብ አመሰግናለሁ። ፍቅር ያሸንፋል ስንል.?እውነት ያሸንፋል!
 ውድ የጉራጌ ህዝቦች እና በዚህ ትግል ውስጥ የተሳተፋችሁ ሁሉ የእራስን መብት ለማስከበር የሌሎችን መብት ሳትነኩ ላሳያችሁት ፍፁም ጨዋነት የተሞላበት ሠላማዊ ትግል ክብር ይገባችኋል ። በኢትዮዽያ የፖለቲካ ትግል ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ ከፍታችኋል።በጉራጌ ሀዘን ኢትዮዽያ አትደሰትም! ፍትህ ለጉራጌ ህዝብ! እኔም ጉራጌ ነኝ። በማለት ሐሳባቸውን ጨርሷል። ወደ ሰሚር አብዱ ሐሳብ ስናልፍ ብልፅግና የሌሎች የክልል ጥያቄ የዲሞክራሲ ማሳያ ነው ካለ የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ በኮማንድ ፖስት አጥሮ በሀገር መከላከያ ለማፈን መሞከር የምን ማሳያ እንበለው። ህገ መንግስቱ ይከበር ። መንግስት የጉራጌ ህዝብ ንቆ የትም ።የህዝብ ድምፅ ይከበር። ብሏል። መስፍን ሚኪኤል በበኩላቸው የምን ክላስተር?  በሚል ጥያቄ ሐሳባቸውን ይጀምሩና ቀጠሉ ቤተጉራጌን ክልል ለማድረግ መንግስት ይቸገራል ማለትስ ምን ማለት ነው? ታዲያ ለሌላው ክልል ለመስጠት መንግስት ለምን አልተቸገረም? በእኔ ግምት የመንግስት መልስ ትክክል አይደለም:: ስለዚህ መንግስት ህዝቡ የሚፈልገው የክልልነት ጥያቄ በፍጥነት ተቀብሎ ህዝቡ ተረጋግቶ ወደ ልማት እና ወደ ብልጽግና ጎዳና እንዲሄድ በፍጥነት መስራት አለበት:: ለቤተጉራጌ ክልል ቢሰጠው ተገቢ ነው:: ምክንያቱም ለበለጠ ስራ ይነሳሳልና። ሲቀጥል  ከሁሉ ኢትዮጵያውያን ጋር በፍቅር አብሮ ይሰራል::

Symbolbild | Twitter Logo - Elon Musk
ምስል Stanislav Kogiku/picturedesk/picture alliance

የፌደራል መንግስትና የትግራይ ክልል ያካሂዱታል ተብሎ የታሰበውና ተስፋን ጭሮ ግን ብዙም ፈቀቅ ያላለው ድርድር በተመለከተም ትኩረት ከተሰጣቸውና በርካታ የማሕበራዊ መገናኛ ብዙሃን ተጠቃሚዎች አስተያየቶች የተስተናገደበት ነበር። ራዕይ የተጋሩ ኢትዮጵያውያን ሀገር አቀፍ ህዝባዊ ንቅናቄ የተባለው የፖለቲካ ድርጅት በፌዴራል መንግሥትና በሕወሓት መካከል ሊደረግ በታሰበው ድርድር ውስጥ ተሳትፎ ሊኖረኝ ይገባል ሲልም ጠይቋል። ፓርቲው በተለይ ለምክትልና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን እንዲሁም ለአፍሪካ ሕብረትና ለምዕራባዊያን አገራት ተወካዮች ይህንኑ በመጠየቅ ደብዳቤ ልኳል። ሌሎች በትግራይ ስም የተደራጁ 3 ፓርቲዎችም ህወሐት ብቻውን የመደራደር ሃላፊነትም ብቃትም የለውም በማለት በሰፊው ጽፈዋል። በዚህ ላይ ተንተርሰው ከተሰጡ አስተያየቶች የተወሰኑ ሐሳቦች እናቀርባለን። ኑሩ ሑሴን  መሰረታዊ ኣገልግሎቶች መልቀቅ ግድ ነው።በዓለም ተደርጎ የማይታወቀው ኢትዮጵያ ላይ ለምን ይሞክራሉ ። የሚል አጭር አስተያየት ሲያስቀምጡ ሰይድ መሀመድ ደግሞወይ ይህ ድርድር መቼ ነው የሚጀመረው ?? ህዝባችን ሠላም አንድነት ይፍልጋል ።እኔን ጨምሮ ግን ፖለቲከኞች ድርድሩን ማራዘማቸው ለምን አስፈለገ በማለት ይጠይቃሉ። ብርሃነመስቀል ታመነ ፍህትም ድርድር የምል ቀልድ ነው እንጅ እውነተኛ አይደለም። ብሏል ጊዜ ለኩሉ ወይ ድርድር ቆይ ብልፅግና የሚያቀርበው መደራደሪያ ምን ይሆን ምን ሊቀበል ይሆን ጉድ አይ ሰሜን እዝ። ብሏል። ኢብራሂም አብዱ ሌላው ሊሟላ ይችላል። ግን የባንክ አገልግሎቱ የድርድሩ ውጤት ከታየ በሁዋላ መሆን አለበት። እንደፍቃድህ ይሁን የተባሉ በፌስቡክየትግራይ ስራዊት ሲባል ትግራይ ሉላዊት ሀገር ነች ለማለት ይሆንን? ከሆነስ ትግራይ ከኢትዮጵያ ልትገነጠል ማለት ነዉ የገባዉ ካለ ግልጽ ቢያደርግልኝ ደስ ይለኛ አመሰግናለሁ።ሃሰን ናስረላህ በበኩላቸው ``የትግራይ ሰራዊት ትጥቅ ፈቶ በአንድ ኢትዮጵያ መንግስት ስር ካልተዳደረ የኢትዮጵያ ህዝብም ለድርድሩ ፍቃደኛ አይደለም።``
በዚሁ እንግዲህ የዛሬውን ዝግጅታችንን አጠቃለናል።

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር 

እሸቴ በቀለ