1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ መንግሥት አመሰራረትን ሦስት ፓርቲዎች ተቹ

ዓርብ፣ የካቲት 10 2015

ትግራይ ክልል ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የትግራይ ክልል ጊዜያዊ መንግሥት አመሰራረት ላይ እምነት እንደሌላቸው ሦስት ፓርቲዎች ተናገሩ።

https://p.dw.com/p/4NfHH
Kenia I Friedensabkommen von Pretoria
ምስል Yasuyoshi Chiba/AFP/Getty Images

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ መንግሥት ጉዳይ

 ትግራይ ክልል ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የትግራይ ክልል ጊዜያዊ መንግሥት አመሰራረት ላይ እምነት እንደሌላቸው ተናገሩ። ዓረና ትግራይ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ እንዲሁም የናፅነት ትግራይ ፓርቲ አመራሮች  በትግራይ ክልል የሚመሰረተውን ጊዜያዊ ክልላዊ መንግሥት በሚያቋቁመው ኮሚቴ ላይ እምነት እንደሌላቸው ግንኙነትም እንደማይኖራቸው ለዶቼ ቬሌ ገለፁ

የዓረና ትግራይ ፓርቲ የኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ካህሳይ ዘገየ ሁሉንም የፖለቲካ ፓርቲዎች አካታች መሆን ሲገባው አሁን እየተሠራ ያለው ሥራ  እኛን ያካተተ አይደለም ይላሉ « ስምምነቱ  አካታች የሽግግር መንግስት ነው የሚለው እየተደረገ ያለው ግን እኛን ያገለለነው» ሲሉ አያይዘውም ምላሽ ለማግኘት ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ባለስልጣናትን ቢጠይቁም ምላሽ ማግኘት አልቻልንም ብለዋል አሁን ላይ የተመረጡትን ዘጠኝ ሰዎችን አንቀበልም ብለዋል።

አቶ ካህሳይ ዘገየ ለሚመለከተው ባለስልጣናትም ለፌደራል መንግስት ማሳወቃቸውን ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል «እኛ ለጠቅላይ ሚኒስቴሩ የደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በጠሩት ስብሰባ ላይም ሀሳባቸንን አቅርበናል» ብለዋል ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ(ህወሓት) አሁንም አምባ ገነናዊ ስርዐት ነው በማስኬድ ላይ ያለው ብለዋል

«ኮሚቴው እየሠራ ያለው የህውሀትን ሀሳብ ነው» የሚሉት ሌላው የናፅነት ትግራይ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዶ/ር ደጀን መዝገበ  ከተመረጡት ሰዎች ጋር ምንም አይነት ችግር የለብንም ነገር ግን መወከል ያለበት አማራጭ ሀሳብ ነው አሁንግን አንድ ቡድንን ለመጥቀም የሚሰራ ስራ ስለሆነ በዚህ መንገድ ህዝባችንን ማዳን ስለማንችል  ሙሉ ለሙሉ እዚህ ላይ ተሳታፊ መሆን አንፈልግም ብልዋል አክለውም «የራሳችን የሆነ ሌላ አማራጭ ግን በቅርቡ ይዘን እንመጣለን» ሲሉ ሃሳባቸውን ሰተዋል

 የሳልሳዊ ወያኔ ትግራይ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ክንፈ ሐዱሽ በበኩላቸው የተቋቋመው ኮሚቴ ሕጋዊ መሠረት የለውም ባይ ናቸው። ከዚህም ሌላ አካታች ባለመሆኑ ለእነሱም ሆነ ለህዝባቸው ምንም ለውጥ በማያመጣ ሂደት ውስጥ መሳተፍ እንደማይፈልጉ ተናግረዋል። አቶ ክንፈ እንደሚሉት «የተመረጡት ዘጠኝ ሰዎችን ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የመረጣቸው እንጂ ምሁራን ተሰብስበው የወከሉት አንድም ሰው የለም አሁን የሚፈለፈው ለይስሙላ ፓርቲዎች እንድንሳተፍ ነው እኛ ደግሞ በዚ መንገድ መሳተፍ አንፈልግም» ብለዋል ። አያይዘውም እየተሰራ ያለው ስራ ለኛም ለህዝባችንም የሚጠቅም ስራ አይደለም ስዚህ አንሳተፍም ብለዋል ።  

ከትናንት በስተያ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ ክልላዊ መንግሥት ለማቋቋም ኮሚቴ ተዋቅሮ እየተሠራ መሆኑን የኮሚቴው ሰብሳቢ ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ ተናግረዋል ጀነራሉ ኮሚቴው ዘጠኝ አባላት እንዳሉት መናገራቸውም ይታወሳል።

ማኅሌት ፋሲል 

ሸዋዬ ለገሰ