1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የትግራይ አስተዳደር ዕጣ ፈንታ

ሐሙስ፣ ኅዳር 4 2012

ህወሓት ፓርቲ ልሳን የሆነው ወይን መፅሔት መጪው ሀገራዊ ምርጫ ሳይካሄድ ከቀረ ቀጥሎ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ፈተናዎች ለማለፍ ትግራይ አብዝሀ የምሉእ መንግስትነት ቅርፅ የያዘ ግን ደሞ ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነት የሌለው መንግሥት ማለትም 'Defacto state' ሆና መቆየት አለባት የሚል ሀሳብ ይዞ ቀርቧል።

https://p.dw.com/p/3T3YQ
Äthiopien Stadtansicht Mekele
ምስል DW/M. Hailessilasie

«ዓለም አቀፍ ተቀባይነት የሌለው መንግሥት ጉዳይ እያነጋገረ ነው»

ህወሓት ፓርቲ ልሳን የሆነው ወይን መፅሔት መጪው ሀገራዊ ምርጫ ሳይካሄድ ከቀረ ቀጥሎ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ፈተናዎች ለማለፍ ትግራይ አብዝሀ የምሉእ መንግስትነት ቅርፅ የያዘ ግን ደሞ ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነት የሌለው መንግሥት ማለትም 'Defacto state' ሆና መቆየት አለባት የሚል ሀሳብ ይዞ ቀርቧል። በትግራይ የሚንቀሳቀሱ አንዳንድ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችና ሌሎች ልሂቃንም ይህንኑ ሐሳብ ሲያነሱ ቆይተዋል። በሌላ በኩል ተቃዋሚው ዓረና ትግራይ ጨምሮ ሌሎች ፖለቲከኞች ግን አካሄዱ አይቀበሉትም። ሚሊየን ኃይለ ሥላሴ ከመቀሌ ዝርዝሩን ልኮልናል። 

ሚሊየን ኃይለ ሥላሴ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ