1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የትግራይ ቴሌቭዥን ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደና ጓደኛው በመቐለ ከተማ ተገደሉ

ረቡዕ፣ ጥር 12 2013

የትግራይ ክልላዊ መንግሥት የሚያስተዳድረው ቴሌቭዥን ጣቢያ ጋዜጠኛ የነበረው ዳዊት ከበደ እና ጓደኛው ትናንት በመቐለ ከተማ በጥይት ተመተው ተገደሉ። ቤተሰቦቻቸው እና የሥራ ባልደረቦቻቸው እንደተናገሩት ዳዊት እና ጓደኛው የተገደሉት የሰዓት ዕላፊ በታወጀባት ከተማ በተሽከርካሪ ሲንቀሳቀሱ ከጸጥታ ኃይሎች በተከተኮሰ ጥይት ነው።

https://p.dw.com/p/3oBJ6
Äthiopien Tigray | Hauptstadt Mekele
ምስል imago images/GFC Collection

ከሚሊዮን ኃይለስላሴ ጋር የተደረገ አጭር ቃለ ምልልስ

የትግራይ ክልላዊ መንግሥት የሚያስተዳድረው ቴሌቭዥን ጣቢያ ጋዜጠኛ የነበረው ዳዊት ከበደ እና ጓደኛው ትናንት በመቐለ ከተማ በጥይት ተመተው ተገደሉ።  የሟች ቤተሰቦች እና ጓደኞች ለዶይቼ ቬለው የመቐለ ዘጋቢ ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ እንደተናገሩት ጋዜጠኛ ዳዊት እና አንድ ሌላ ጓደኛው በከተማው በተሽከርካሪ በመንቀሳቀስ ላይ ሳሉ ከጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተገድለዋል። በተሽከርካሪው ውስጥ የነበሩ ሌሎች ሁለት ሰዎች ደግሞ ታስረዋል። በመቐለ ከተማ የሰዓት ዕላፊ ታውጇል። ወደ ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት ያነጋገርኩት ሚሊዮን እንደነገረኝ ኩነቱ የተፈጸመው በከተማው መንቀሳቀስ በተከለከለበት ወቅት ነው። የትግራይ ፖሊስ ኮሚሽን እና ከጊዜያዊው አስተዳደር ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ሚሊዮን ያደረገው ጥረት እንዳልሰመረ በስልክ ነግሮኛል። ከሚሊዮን ኃይለስላሴ ጋር የተደረገውን አጭር ቃለ መጠይቅ ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ

ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ
እሸቴ በቀለ
ሸዋዬ ለገሠ