የትግራይ መልሶ ግንባታ
ማክሰኞ፣ ኅዳር 29 2013ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የፌደራል መንግስት በቅርቡ በተደረገዉ ጦርነት የተጎዳዉን የትግራይን የመሰረተ ልማት አዉታርን ባፋጣኝ መገንባት እንዳለበት ሁለት ሙሑራን መከሩ። የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሥነ መንግሥትና የሕግ መምሕራን እንደሚሉት በክልሉ ዘላቂ ሠላም ለማስፈንና ሕጋዊ አስተዳደር ለመመስረት መንግሥት ከአካባቢዉ ተወላጆች ጋር «ሠፊ» ያሉትን ዉይይትና ንግግር ማድረግ አለበት። የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደርን ማጠናከር፣ ፀጥታን ማስከበርና መገናኛ ዘዴዎች አካባቢዉን እንዲጎበኙ መፍቀድ እንዳለበትም ምሑራኑ አስታዉቀዋል።
ስዩም ጌቱ
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ