1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 የትግራዩ  ጦርነትና የኮሎኔሉ አስተያየት

ረቡዕ፣ ኅዳር 16 2013

በሚንስቴሩ የሕብረት ሎጂስቲክስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ኮሎኔል ሹማ ኦብሳ  በተለይ ለዶይቼ ቬለ እንደነገሩት ወታደራዊ ዘመቻዉ "መገባደጃና መጨረሻዉ ምዕራፍ ላይ ደርሷል

https://p.dw.com/p/3lp1L
Äthiopien Armeesprecher | Militär kreist Mekele Tigray ein
ምስል Seyoum Hailu /DW

በትግራዩ ጦርነት የመከላከያ ሠራዊት ጥንቃቄ

 የኢትዮጵያ ፌደራዊ መግሥት ጦር ትግራይ ዉስጥ «ሕግ ለማስከበር» ያለዉ የጦር ዘመቻ የመጨረሻ ግብ  በክልሉ ዘላቂ ሠላምና መረጋጋት ማስፈን እንደሆነ የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።በሚንስቴሩ የሕብረት ሎጂስቲክስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ኮሎኔል ሹማ ኦብሳ  በተለይ ለዶይቼ ቬለ እንደነገሩት ወታደራዊ ዘመቻዉ "መገባደጃና መጨረሻዉ ምዕራፍ ላይ ደርሷል።የፌደራሉ መንግስት ጦርና የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ ታጣቂዎች በገጠሙት ጦርነት ሠላማዊ ሰዎች እንዳይጎዱ ጥንቃቄ ያደርጉ ዘንድ የተለያዩ ዓለም አቀፍ የመብት ተሟጋች ድርጅቶች እየተማፀኑ ነዉ።ኮሎኔል ሹማ እንደሚሉት ጦራቸዉ ሰላማዊ ዜጎችን ከታጣቂዎች «ለመለየት» አበክሮ ይጥራል።

ስዩም ጌቱ 

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ