1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የትግራዩ ጦርነት፣ የአቶ ዩሱፍ ያሲን አስተያየት

ሰኞ፣ ኅዳር 14 2013

ዉጊያዉ ራሱ ሕወሓት በኢትዮ-ኤርትራዉ ጦርነት ያፈራቸዉ የጦር አለቆች፣ በርዕዮተ ዓለሙ ያጠመቃቸዉ፣ ለመሪነት ያበቃቸዉ ፖለቲከኞች ከሚያዙት ጦር ጋር መሆኑ ነዉ የ1990ዉን ግራ አጋቢ ታሪክ የመደገሙ አብነት።ያስደንቅ፣ ያስደነግጥ፣ያሳስብ ይሆን? የቀድሞዉ ዲፕሎማት፣ ደራሲና የፖለቲካ ተንታኝ ዩሱፍ ያሲን «አይ አዎ» ነዉ መልሳቸዉ።     

https://p.dw.com/p/3ljLF
Yousuf Yasin | Analyst | Buch
ምስል Negash Mohammed/DW

«በጠመንጃ ስልጣን የመነጣጠቅ አባዜ» የሱፍ ያሲን

ኢትዮጵያ ጦረኝነት-ከበሳል ፖለቲከኝነት፣ መገንጠልን-ከአንድነት፣ የትግራይ ብሔርተኝነትን-ከኢትዮጵያዊነት፣ ኮሚንስትነትን-ከካፒታሊስትነት፣ ብቸኛ ገዢነትን-ከመድብለ ፓርቲ ሥርዓት አቀንቃኝነት ጋር የቀየጠ ፓርቲ ከነበረና ካላት እሱ፣ ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ነዉ። ያ ጠንካራ የጦር ማሕበር ጫካ በነበረበት ዘመን እንደሱዉ ሁሉ ደርግ መራሹን የኢትዮጵያ መንግስትን ለመዉጋት ጫካ ከገቡት፣ ከግንባር ገድሊ ሓርነት ትግራይ (ግገሓት) እስከ ጀበሐ፣ ከኢዲዮ እስከ ኢሕአፓ ከነበሩ አማፂያን ጋር ተዋግቷል።በየዉጊያዉም፣ በሴራም፣በደባም እያለ ሁሉንም ተራ በተራ አሽነፏል።-----ሕወሓት ዛሬም ጦርነት ላይ ነዉ።ዉጊያዉ ራሱ ሕወሓት በኢትዮ-ኤርትራዉ ጦርነት ያፈራቸዉ የጦር አለቆች፣ በርዕዮተ ዓለሙ ያጠመቃቸዉ፣ ለመሪነት ያበቃቸዉ ፖለቲከኞች ከሚያዙት ጦር ጋር መሆኑ ነዉ የ1990ዉን ግራ አጋቢ ታሪክ የመደገሙ አብነት።ያስደንቅ፣ ያስደነግጥ፣ያሳስብ ይሆን? የቀድሞዉ ዲፕሎማት፣ ደራሲና የፖለቲካ ተንታኝ ዩሱፍ ያሲን «አይ አዎ» ነዉ መልሳቸዉ።    

ነጋሽ መሐመድ