1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በዘ ሄግ የተከሰሱት የአቶ እሸቱ ዓለሙ ጉዳይ

ረቡዕ፣ ጥቅምት 22 2010

ተከሳሹ አቶ እሸቱ ዓለሙ የኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም መንግሥት ተቃዋሚዎች በቀይ ሽብር አማካኝነት ይገድል፣ ያሥር እና ያሰቃይ የነበረበትን አሠራር ተግባራዊ አድርገዋል በመባል ነው በቀይ ሽብር ወንጀለኝነት የተከሰሱት።

https://p.dw.com/p/2ms5V
Justitia mit Pendelwaage
ምስል picture-alliance/Ulrich Baumgarten

የትውልደ ኢትዮጵያዊ ሆላንዳዊው የቀይ ሽብር ክስ በዘሄግ

በትውልደ ኢትዮጵያ ሆላንዳዊው አቶ እሸቱ ዓለሙ ላይ የቀረበው የቀይ ሽብር ወንጀል ክስ ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ዘሄግ ኔዘርላንድስ ውስጥ እየታየ ነው። ተከሳሹ አቶ እሸቱ ዓለሙ የቀድሞ የደርግ አባል እንዲሁም የጎጃም ክፍለ ሀገር ከፍተኛ ባለሥልጣን በመሆን ማገልገላቸዉ ተገልጿል። የኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም መንግሥት ተቃዋሚዎች በቀይ ሽብር አማካኝነት ይገድል፣ ያሥር እና ያሰቃይ የነበረበትን አሠራር ተግባራዊ አድርገዋል በመባል ነው በቀይ ሽብር ወንጀለኝነት የተከሰሱት። 

ገበያው ንጉሴ

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሰ