1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ደጋፊዎቹ እስራኤልና ሳዑዲ አረቢያ ብቻ ናቸዉ

ረቡዕ፣ ግንቦት 1 2010

የተቀረዉ ዓለም ዉሳኔዉ ዲፕሎማሲያዊ ድርድርን ዋጋ የሚያሳጣ፤ ዓለም አቀፍ ሠላምን የሚያወክ በማለት ቅሬታዉን እየገለጠ ነዉ።ሥምምነቱን የፈረሙት ራስዋ ኢራን፤ ሩሲያ፤ ቻይና፤ ብሪታንያ፤ ፈረንሳይ፤ ጀርመን እና የአዉሮጳ ሕብረት ዉሉ እንደማይፈርስ አስታዉቀዋል

https://p.dw.com/p/2xRfk
USA Trump verlässt den Raum ARCHIV
ምስል picture-alliance/NurPhoto/C. May

(Beri.Brussels) Reax on Trumps Decision - MP3-Stereo

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የኢራንን የኑክሌር መርሐ-ግብር ያስቆመዉን ሥምምነት ማፍረሳቸዉን ከሁለት ሐገራት በስተቀር መላዉ ዓለም ተቃወመዉ። የትራምፕን እርምጃ የደገፉት እስራኤል እና ሳዑዲ አረቢያ ብቻ ናቸዉ። የተቀረዉ ዓለም ዉሳኔዉ ዲፕሎማሲያዊ ድርድርን ዋጋ የሚያሳጣ፤ ዓለም አቀፍ ሠላምን የሚያወክ በማለት ቅሬታዉን እየገለጠ ነዉ። ሥምምነቱን የፈረሙት ራስዋ ኢራን፤ ሩሲያ፤ ቻይና፤ ብሪታንያ፤ ፈረንሳይ፤ ጀርመን እና የአዉሮጳ ሕብረት ዉሉ እንደማይፈርስ አስታዉቀዋል። እንደ ጎርጎርያኑ አቆጣጠር በ2015 የተፈረመዉ ሥምምነት በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት የፀደቀዉ ዉል ነዉ።የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል። 

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ