1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የታንዛንያ ምርጫ እና ዉዝግቡ  

ቅዳሜ፣ ጥቅምት 21 2013

በያዝነዉ ሳምንት ረቡዕ በታንዛንያ የተካሄደዉ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ገዥዉ የፕሬዚዳንት ጆን ማጊፉሊ ፓርቲ  ማሸነፉ የምርጫዉ ዉጤት በይፋ ከመነገሩ ቀደም ሲል ጀምሮ እየተበሰረ ነበር። ይሁንና የተቀናቃኝ ፓርቲ ዉጤቱ ተጭበርብሮአል ፤ ምርጫዉም  ሕገ-ወጥ ነዉ ሲል ሲል እያወገዘ ነዉ።

https://p.dw.com/p/3kgGT
Tansania Sansibar | Wahlen | Bevölkerung geht Wählen
ምስል Patrick Meinhardt/AFP/Getty Images

ተቃዋሚዎች «ምርጫዉ ተጭበርብሮአል እዉቅና አትስጡ»


በያዝነዉ ሳምንት ረቡዕ በታንዛንያ የተካሄደዉ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ገዥዉ የፕሬዚዳንት ጆን ማጊፉሊ ፓርቲ  ማሸነፉ የምርጫዉ ዉጤት በይፋ ከመነገሩ ቀደም ሲል ጀምሮ እየተበሰረ ነበር። ይሁንና የተቀናቃኝ ፓርቲ ዉጤቱ ተጭበርብሮአል ፤ ምርጫዉም  ሕገ-ወጥ ነዉ ሲል ሲል እያወገዘ ነዉ። አብዮታዊዉ የሚባለዉ « ቻማ ቻ  ማፒንዱዚ» የተሰኘዉ የፕሬዚዳንት ጆን ማጊፉሊ ፓርቲ  ታንዛንያ ከብሪታንያ ቅኝ ግዛት ከተላቀቀችበት ከጎርጎረሳዉያኑ 1961 ዓ.ም ጀምሮ ስልጣን ላይ ይገኛል። ረቡዕ በተካሄደዉ ምርጫ  የፕሬዚዳንት ማጊፉሊ ፓርቲ ከፊል ራስ ገዝ በሆነችዉ ዛንዚባር ከ 76.2 በመቶ በላይ ድምፅን ማግኘቱን እያበሰረዉ ምርጫዉ በተካሄደ በነጋታዉ ነበር ። ከመርጫዉ አንድ ቀን ቀደም ብሎ በዛንዚባር ከ10 በላይ የሚሆኑ የተቃዋሚ ፓርቲ ባለስልጣናት እና አባላት ታስረዋል። በፖሊስ ድብደማ ከደረሰባቸዉ መካከል ተቃዋሚዎች ላይ ቢያንስ አንድ ሰዉ  ክፉኛ ተጎድቶ ። በፕሬዝደንታዊዉ ምርጫ ድምፅ ከተሰጠባቸዉ 264 የምርጫ ጣቢያዎች መካከል እስከ ትናንት አርብ ምሽት ድረስ 80 ዉጤት በይፋ ተነግሯል። ከተቆጠረዉ ድምፅ ለሁለተኛ ዘመነ ሥልጣን የተወዳደሩት ጆን ማጉፉሊ 85 ከመቶዉን አግኝተዋል። 200 መቀመጫዎች ላሉት ምክር ቤት በተደረገዉ ፉክክር ደግሞ ገዢዉ ፓርቲ ቻማ ቻ ማፒንዱዚ (CCM) ከ2ቱ  በስተቀር የተቀሩትን 180 መቀመጫዎች በእጁ አስገብቶአል። 
የማጉፉሊ ዋነኛ ተቀናቃኝ የቻዴማ ፓርቲ ዕጩ ታንዱ ሉዊስ ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የምርጫዉ ሒደት በሁሉም ደረጃ የተጭበረበረ ነዉ።  
«የተጭበረበረ» በማለት ዉጤቱን ዉድቅ አድርገዉታል። የማጉፉሊ ዋነኛ ተቀናቃኝ የቻዴማ ፓርቲ ዕጩ ታንዱ ሉዊስ ትናንት እንዳሉት የምርጫዉ ሒደት በሁሉም ደረጀ የተጭበረበረ ነዉ።«ከትናንቱ ምርጫ አንዱንም አንቀበልም።ምክንያቱም በሁሉም ደረጃ የነበረዉ ሒደት የተጭበረበረ ነዉ። እንዳልኩት ታዛቢዎቻች በየምርጫ ጣቢያዉ እንዳይገቡ ታግደዋል። ሥለዚሕ አቋማችን ለዉጤቱ ምንም ዓይነት ዕዉቅና አለመስጠት ነዉ።» 
በዛንዚባር  አምስት ክልሎች በተደረገዉ ምርጫ እና ድምፅ አሰጣጥ ተመሳሳይ ሁኔታ ታይቶአል። በዛንዚባር  ተቃዋሚዎች ሰፊ መቀመጫን ይገኛሉ  ተብሎ በሚታመንበት በፔብባ ደሴት፤ የታንዛንያ ዋነኛዉ ተቀናቃኝ የሆነዉ የቻዴማ ፓርቲ ሽንፈት እንደደረሰበት የተነገረዉ በምርጫዉ ማግስት ነበር። በዛንዚባር ACT ዋዛላንዶ የተሰኘዉ ተቃዋሚ  ፓርቲ  መሪ እና የፕሬዚዳንታዊ  እጩ ሴይፍ ሻሪፍ ሀማድ ፓርቲያቸው ከመቼውም ጊዜ የከፋ ነው ያለውን ይህን አጠቃላይ የምርጫና  ዉጤቱን  እንደማይቀበል ብሎም በአደባባይ ከፍተኛ ተቃዉሞ እንዲደረግ ጥሪ አስተላልፈዉ ነበር።  
«ሰዎች ያለአንዳች መሳርያ ሳይታጠቁ አደባባይ ወጥተዉ ሰራዊቱ ይግደለን ብለዉ ጥሪ ማሰማት አለባቸዉ። እኛ መሪዎች ከተገደልን ጥሪያችን ፤ የዛንዚባር ሕዝብ መብቱን  እስኪያገኝ  ድረስ ፤ ሰላማዊ ትግሉን  እንዲቀጥል ነዉ። »   
የአደባባይ ተቃዉሞዉ ከጀመረ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ የፖርቲ አባላት እና አመራሮች በቁጥጥር ስር ዉለዋል። ከሌሎች የዛንዚባር አካባቢዎች በተለይ ደግሞ ሰፊ የተቃዋሚ ቦታዎች በሚባሉት በፔምባ ደሴት እና በሰሜናዊ ኡንጉጃ የምርጫዉን ሂደት እና ተገኘ የተባለዉን ዉጤት በመቃወም በተካሄደ የአደባባይ ሰልፍ  ሲቪሎች ተደብድበዋል ከ 10 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸዉን አጥተዋል። ፖሊስ በበኩሉ በተቃዋሚዎች ላይ አልተኮስኩም ሲል ድርጊቱን አስተባብሎአል።  የዛንዚባር ነዋሪዉ ሃማድ በፖሊስ በቁጥጥር ስር ከመዋሉ በፊት የዘንድሮ የታንዛንያ ጠቅላላ ምርጫ ፤ ወታደራዊ ስልጠና እንጂ ፤ ሕዝባዊ ምርጫ አልነበረም ብሎታል።   
«በዋናዉ የሃገሪቱ ክፍል ላይ ምርጫ ተካሂድዋል ። ነገር ግን በምርጫ ጣብያዎች አንድም ወታደር አላየንም። በዛንዚባር ግን ምርጫ ጣብያዎች ሁሉ በጦር ሰራዊት ተከበዉ ነበር። በዋናዉ የሃገሪቱ ክፍል ላይ የሚሆነዉና በዛንዚባር የሚታየዉ ነገር የተለያየ ነዉ። ልክ ዛንዚባርን  በቅኝ ግዛታቸዉ እንደያዝዋት ያህል ፤ ዛንዚባርን እንለቃለን ብለዋል። » 
የሃማድ ደጋፊ የሆኑት  ሊሱ በበኩሉ « የተሰረቀዉ የሚሊዮኖች ተስፋ» በሚል በፕሬዚዳንት ማጊፉሊ እና መንግሥታቸዉ ላይ  ሰላማዊ የተቃዉሞ ሰልፍ እንዲወጣ ጥሪ ፤ አቅርበዋል።  ዓለም አቀፍ ተቋማትም በታንዛንያ ይፋ የሆነዉን የምርጫ ዉጤት እዉቅና እንዳይሰጡ ፤ መንግሥት ነኝ ከሚለዉም እንዳይተባበሩ ጥሪ አስተላልፈዋል።    
«ክልላዊ እና ዓለማቀፋዊ ድርጅቶች የምርጫ ታዛቢዎችን እንዲልኩ ጠይቀናል።  በተለይ ደግሞ የአፍሪቃ ኅብረት ይህን ሕገ-ወጥ ዉጤት እዉቅና እንዳይሰጥ ጥሪ አቅርበናል። የታንዛኒያ ወዳጆች ይህን ምርጫ እንዲቆጣጠሩ ተልእኮ ተሰጥቷቸው ከነበሩት ጋር ሆነዉ፤ በታንዛኒያ መንግስት ላይ የሚቻላቸዉን ማንኛውንም ጫና እንዲያደርጉ እንጠይቃለን ፣ ይህ የምርጫ እንዲጭበረበር  ባደረጉት ወይም ባዘዙት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ እንጠይቃለን።»
ይህ ጥሪ በተለይ ደግሞ በዛንዚባር ተቀባይነት የማግኘት ተስፋዉ የመነመ ነዉ። በዛንዚባር የታንዛንያ የሴትች  ሚዲያ ማኅበር በዚህ የምርጫ ማጭበርበር ሂደት በሃገሪቱ የነበሩት ጥቃቅኖቹ የእርቅ ተስፋዎች ሁሉ ተሟጠዉ ጠፍተዋል። 
የፖለቲካ ጉዳዮችን ወደ ጠላትነት መንፈስ በመቀየራቸዉ በተለይ ይህ ምርጫ በመጥፎ ሁኔታ ነዉ የተካሄደዉ። ስለሆነም እርቁን የዛንዚባር ነዋሪዎች  ቢፈልጉ  እንኳ በሁለቱም ተፎካካሪ ፓርቲዎች መካከል እርቅ የሚፈጠር አይመስልም። ነገር ግን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጣልቃ ቢገባ፤ የሆነ ነገር ሊከሰት ይችል ይሆናል። ግን የሚሆን አይደለም። 

Tansania Daressalam Präsidentschaftskandidat Bernard Membe und Omary Fakiy
ምስል Said Khamis/DW
Tansania Daressalam Präsidentschaftskandidat Bernard Membe und Omary Fakiy
ምስል Said Khamis/DW


አዜብ ታደሰ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ