1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የታኅሣሥ 4 ቀን፣ 2014 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 4 2014

እጅግ ብርቱ ፉክክር በታየበት አወዛጋቢው የአቡዳቢ የፎርሙላ አንድ የመኪና ሽቅድምድም የመርሴዲሱ አሽከርካሩ ሌዊስ ሐሚልተን በሆላንዳዊው የሬድቡል አሽከርካሪ ማክስ ፈርሽታፐን ድል ኾኗል። በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ ማንቸስተር ሲቲ መሪነቱን እንዳስጠበቀ ነው። በጀርመን ቡንደስሊጋ ባየርን ሙይንሽን በመሪነቱ እየገሰገሰ ነው።

https://p.dw.com/p/44CqM
F1 Saudi Arabian Grand Prix
ምስል Andrey Isakovic/AFP

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

እጅግ ብርቱ ፉክክር በታየበት አወዛጋቢው የአቡዳቢ የፎርሙላ አንድ የመኪና ሽቅድምድም የመርሴዲሱ አሽከርካሩ ሌዊስ ሐሚልተን በሆላንዳዊው የሬድቡል አሽከርካሪ ማክስ ፈርሽታፐን ድል ኾኗል። በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ ማንቸስተር ሲቲ መሪነቱን እንዳስጠበቀ ነው። ሊቨርፑል እና ቸልሲ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ኾነው ይከተላሉ። በጀርመን ቡንደስሊጋ ባየርን ሙይንሽን በመሪነቱ እየገሰገሰ ነው።

Formel 1 | Großer Preis von Abu Dhabi - Lewis Hamilton
ምስል KAMRAN JEBREILI/AFP/Getty Images

ስፔን እና ሜክሲኮ ውስጥ በተከናወኑ የማራቶን ሩጫ ፉክክሮች ኢትዮጵያውያን ድል ቀንቷቸዋል። እንደ ጎርጎሪዮሱ አቆጣጠር ከ2019 ወዲህ በተከናወነው የስፔን ማላጋ የማራቶን ሩጫ ፉክክር በሴቶች ውድድር አትሌት ፀጋነሽ መኮንን አንደኛ ወጥታለች። በአስደናቂ ኹኔታ ባሸነፈችበት ፉክክር 2 ሰአት ከ4 ደቂቃ ከ50 ሰከንድ ሮጣለች። የዐይንአበባ እጅጉ ተከትላት በሁለተኛነት አጠናቃለች። በወንዶች ፉክክር ኬኒያዊው ማርክ ኮሪድ በአንደኛነት ያጠናቀቀው 2 ሰአት ከ7 ደቂቃ ከ40 ሰከንድ በመሮጥ ነው። የኤርትራው ሯጭ ንጉሤ አምሎሶም 2 ሰአት ከ8 ደቂቃ ከ23 ሰከንድ በመሮጥሁለተኛ ደረጃን ይዟል። ኬንያዊው ሌላ ሯጭ ሶሎሞን ኪርዊ በ3ኛነት ውድድሩን አገባዷል። በሜክሲኮ የማራቶን ፉክክር በወንዶች አትሌት ደራራ ደሳለኝ 1ኛ ኾኖ አጠናቋል።  በሴቶች ተመሳሳይ ፉክክር አትሌት አልማዝ ነገደ 3ኛ ደረጃን ይዛለች። ስለኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ለካሜሩን የአፍሪቃ ዋንጫ ዝግጅቱን ለመጀመር ፌዴሬሽኑ 41 ሚሊዮን ብር በጀት እንዲለቅለት እየጠበቀ መሆኑ ተሰምቷል። ስለ ቡድኑ ቅድመ ዝግጅት እና አጠቃላይ መሰናዶ ቃለ መጠይቅ አድርገናል።ሙሉ ዝግጅቱን በድምፅ ከማጫወቻው ማግኘት ይቻላል። 

ማንተጋፍቶት ስለሺ

አዜብ ታደሰ