የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዉዝግብ
ቅዳሜ፣ ሰኔ 5 2013ማስታወቂያ
በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ውዝግብ ዙሪያ ግብፅና ሱዳን የሚከተሉት አቋም የተሳሳተና ችግሩን የሚያባብስ መሆኑን ዶቼ ቨለ ያነጋገራቸው የፖለቲካ ሳይንቲስት ገለፁ። በሞርጋን ስቴት ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንቲስት ዶክተር ጌታቸው መታፈሪያ እንደተናገሩት የሃገራቱ አቋም በአፍሪካውያንና በአረቦች መካከል ቁርሾን የሚፈጥር ነው። ሱዳንና ግብፅ ሰሞኑን በጋራ ባወጡት መግለጫ የሕዳሴ ግድቡን ውዝግብ ለመፍታት የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጣልቃ እንዲገባ ጠይቀዋል።
ታሪኩ ኃይሉ
አዜብ ታደሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ